ኢትዮጵያ መድን ሀሰን በሽር ረዳት አሰልጣኝ ሀብቶም ቢሰጠኝን ደግሞ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በማድረግ ሾሟል።

በአዲሱ አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ መሪነት በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን እያከናወነ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን የክለቡን መለያ ለብሶ በ1990 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ጎል አግቢ በመሆን የጨረሰው እና ባለፉትን አመታት ከወጣት ቡድኑ እስከ ዋናው ድረስ ረዳት አሰልጣኝ እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በመሆን ያገለገለው የቀድሞው አንጋፋ አጥቂ ሀሰን በሽር ረዳት አሰልጣኝ የቀድሞው የትራንስ ፣ ሀዋሳ ፣ ወልዋል እና ደደቢት እንዲሁም በቅርቡ በመቐለ ከተማ ወጣት ፕሮጀክት ላይ ሲሰራ የነበረውን የቀድሞው ግብ ጠባቂ ሀብቶም ቢሰጠኝን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በማድረግ ክለቡ ሾሟል።
አስተያየት ይስጡ