የሀድያ ሆሳዕና ቡድን የባህር ዳር ጉዞ ?

በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በጠንካራ ግስጋሴ የውድድር ዓመቱን የጀመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች በመጪው ቅዳሜ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ጨዋታቸውን ቢያደርጉም ቡድኑ አለመሰባሰቡ ተገልጿል ።

ሀትሪክ ስፖርት ከውስጥ ምንጮች ለማወቅ እንደቻለችው ቡድኑ በተለያዩ ቦታዎች ተበታትኖ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል ። የሀድያ ሆሳዕና ቡድን ልምምድ ከሰሩ መሰነባበታቸው ሲታወቅ በአስራ አንደኛ ሳምንት ከ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጋር አንድ አቻ በወጡበት ጨዋታም ልምምድ አለመስራታቸውንም ለማወቅ ችለናል ።

ቡደኖች ከወዲሁ ቀጣይ መርሐ ግብሮች ወደ ሚካሄድበት ባህርዳር ከተማ ሲከትሙ የሀድያ ሆሳዕና ተጨዋቾች ከክለቡ አመራሮች የስልክ ጥሪን እየጠበቁ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል ።

ከዚህ በተጨማሪም የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾች የሁለት ወር የደሞዝ ክፍያ እንዳልተፈፀመላቸው ሲታወቅ ቡድኑ በመጪው ቅዳሜ 4:00 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡናን የሚገጥም ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *