መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ጎፈሬ የትጥቅ አምራችና ሀዋሳ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን የ3 አመት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ።
ሀዋሳ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

ጎፈሬ የትጥቅ አምራችና ሀዋሳ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን የ3 አመት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ።

አጋራ
አጋራ

*..ወጣቱ ኮከብም የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል…

ጎፈሬ የትጥቅ አምራችና ሀዋሳ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን የ3 አመት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ።

የጎፈሬ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳሙኤል መኮንን “ከ17 አመት ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን
የልምምድ ፣የጉዞ፣በሜዳና ከሜዳ ውጪ ምግብ መመገቢያ ማሊያና ቱታዎችን እናቀርባለን ውሉ አትሌቲክስ ቡድኑንም የሚመለከት ሲሆን በሶስት አመት ውል መሠረት እስከ 2 ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ዋጋ ያለው ትጥቅ ለክለቡ እናቀርባለን ድርጅታችን በውሉ መሠረት ወደ 10 ሺህ ማሊያ ለደጋፊ ያቀርባል በስምምነቱም ደስተኛ ን” ሲሉ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ስፖርት ክለብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኡቴሳ ኡጋሞ በበኩላቸው “ክለባችን ከታዳጊ ማለትም ከ13 አመት እስከ ዋናው ቡድን በስሩ አቅፏል ለነኚህ ቡድኖች ደግሞ ትጥቅ ከውጭ ስናመጣ ቆይተናል አሁን ግን ጨገር በቀል ከሆነው ጎፈሬ ጋር በመነጋገር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርመናል በቀጣዮቹ ሶስት አመት በጋራ አብረን እንደምንሰራ ተስፋ እናደርጋለን” በማለት ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ጎፈሬ ትጥቅ አምራች ኩባንያም ከአመቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ወጣት ተጨዋች ከሆነው ወንድማገኝ ሃይሉ ጋርም የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል።

ሁለቱ ወገኖች ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት አብረው ለመስራት የተስማሙ ሲሆን ኳስ ተጨዋቾች አምባሳደር መሆን እንደሚችሉ ማሳየትና በይፋ ያልተደረገ ክፍያ በየሶስት ወሩ የሚከፈለው ይሆናል ተብሏል። በውሉ ላይ የባለሙያ ድጋፍና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ተካተውበታል ተጨዋቹም “በስምምነቱ ተደስቻለሁ እንደ ወጣት የተቻለኝን ለማድረግ እጥራለሁ”ብሏል።

ሀዋሳ ከተማ ለወንድማገኝ ከመስከረም ወር ጀምሮ ይከፈለው ከነበረው ደመወዝ አራት እጥፍ እንዲከፈለው መወሰኑም ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...