መነሻ ገጽ አትሌቲክስ ” ህዝቡ አትፈለጊም ስልጣን ልቀቂ ካለ ስልጣኔን በደስታ እለቃለሁ” ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ /የኢት.አትሌቲክስ ፌዴ.ፕሬዝዳንት/
አትሌቲክስዜናዎች

” ህዝቡ አትፈለጊም ስልጣን ልቀቂ ካለ ስልጣኔን በደስታ እለቃለሁ” ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ /የኢት.አትሌቲክስ ፌዴ.ፕሬዝዳንት/

አጋራ
አጋራ

ህዝቡ አትፈለጊም ስልጣን ልቀቂ ካለ ስልጣኔን በደስታ እለቃለሁ”
ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ
/የኢት.አትሌቲክስ ፌዴ.ፕሬዝዳንት/

“ውሻ እንኳን ለሁለት ቤት አይጮህም
ለበላበት ቤት እንጂ”
አቶ ቢልልኝ መቆያ
/የኢት.አትሌቲክስ ፌዴ. ዋና ጸሃፊ/

የአንዳንድ አሰልጣኞች ሁለት ቦታ መርገጥ ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ለኦሎምፒክ ኮሚቴ አለመግባባት መነሻ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የፌዴሬሽኑ የስራ እስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በስካይላይት ሆቴል በሰጡት ሐግለጫ ላይ ዋና ጸሃፊው አቶ ቢልልኝ መቆያ እንደተናገሩት የአንዳንድ አሰልጣኞች ሁለት ቦታ መጮህ ለችግሩ መነሻ መሆኑን ገልጸው ውሻ እንኳን ለሁለት ቤት ሳይሆን የሚጮኸው ለበላበት ነው” ሲሉ እነኚሁ አሰልጣኞችን ወርፈዋል። አቶ ቢልልኝ እንደሚሉት “ኦሎምፒክ ኮሚቴ አሰልጣኞችን አሰለጥናለሁ የሚለው እንዴት ነው? ምናልባት የራሱን ስራ አስፈጻሚ ያሰለጥን ይሆናል”ሲሉ ተሳልቀዋል።

በዚህ መግለጫ ላይ ፕሬዝዳንቷ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እንደተናገረችው “ሃላፊነቴን ስለ መልቀቅ አስቤ አላውቅም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ልቀቂ አትፈለጊም ካለኝ በደስታ እለቃለሁ” ስትል ተናግራለች። “ፌዴሬሽናችን ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ያልተስማማው እልህና እኔ እበልጣለሁ ያመጣው ልዩነት ነው” ያለችው ደራርቱ ” በቶኪዮ ኦሎምፒክ በተመዘገበው ደካማ ውጤት ህዝባችንን ይቅርታ እጠይቃለሁ በውጤቱ ደካማነት ዙሪያ በተፈጠሩ ስህተቶች አሰልጣኞች ሪፖርት እንዲያቀርቡ አዘናል ከሪፖርቱ በኋላ ርምጃ እንወስዳለን” ስትልም ፌዴሬሽኑ ጠንካራ አቋም መያዙን ተናግራለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...