በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከዚህ ቀደም የአምስት ተጫዋቾችን ፊርማ ያገኙት ሀድያ ሆሳዕናዎች በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል ።
ሁለቱም ፈራሚዎች በተጠናቀቀው የውድድር አመት በሰበታ ከተማ ተጫውተው ያሳለፉ ናቸው ።
የመጀመሪያው አማካዩ በኃይሉ ግርማ ሲሆን ከሰበታ ከተማ በፊት በሙገር ሲሚንቶ እና በመከላከያ ተጫውቶ አሳልፏል ። ሁለተኛው ፈራሚ አጥቂው ዘካርያስ ፍቅሬ በአርባምንጭ ከተማ ፤ ሀላባ ከተማ ፤ ድሬደዋ ከተማ እና መከላከያ መጫወት ችሏል ።
ሁለቱም ተጫዋቾች በሀድያ ሆሳዕና መለያ ለአንድ አመት ለመጫወት የሚያስችላቸውን ፊርማ ነው ያኖሩት ።