በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት እየተመሩ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል የቻሉት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከዚህ በተጨማሪም በያዝነዉ ሳምንት የተለያዩ ታዳጊ ተጫዋቾችን ወደ ዋናዉ ቡድን ማሳደጋቸዉ ይታወሳል።
ከአዳዲስ ፈራሚዎች ባሻገርም የነባር ተጫዋቾቻቸዉን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙት ሀድያዎች በዛሬዉ ዕለት የአማካይ ስፍራ ተጫዋቻቸውን ተስፋየ አለባቸዉ(ቆቦ) ለተጨማሪ ሁለት አመት ለማቆየት መስማማታቸዉ ታዉቋል።