ከሳምንታት በፊት ሰርቢያዊውን አሠልጣኝ ዝላትኮ ክራምፖቲች በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ከቀናት በፊት ለፈረሰኞቹ ለመጫዎት ተስማምቶ የነበረዉን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ኢስማኤል አጎሮ ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀላቸዉ ተረጋግጧል።
የ25 ዓመቱ ቶጓዊ በዛሬው እለት በፈረሰኞቹ ቤት ለቀጣዩቹ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ፊርማ ከክለቡ ጋር የተፈራረመ ሲሆን ፤ ተጫዋቹ በነገው እለት ወደ ቢሾፍቱ በማምራት በቅድመ ዉድድር ዝግጅት ላይ የሚገኙትን የፈረሰኞቹ የቡድን አባላት እንደሚቀላቀል ታዉቋል።