“አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና እና ዚምቧቡዌ ጋር ላለበት ጨዋታ በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን በማድረግ ላይ እምደሚገኝ ገልጸው ዝግጅቱ ትኩረት ያደረገው በአካል ብቃት በስነልቦና እና ታክቲካል ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸው።”
“በተለይ off Season በመሆኑ መክንያት ለነዚህ ጨዋታዎች አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶችን በማደረግ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በተለይ የወዳጅነት ጨዋታዎች ከሴራሊዮን እና ከዩጋንዳ ጋር መጫወታችን ራሳችንን በደንብ እንድናይ ያደርገናል።”
“ያለን የስኳድ መጠን ትንሽ ነው። ከሁለቱ ጨዋታዎች በኋላ የመጨረሻ ተጫዋቾችን እናሳውቃለን። ሽመልስ በቀለ የስኳዱ አካል ነው ሌላ ተጫዋቾችን አንጠራም።”
“Off season ላይ ብንሆንም ከልጆቹ ጋር የምንገናኝበት ክትትል የምናደርግበት አማራጭ ስለነበር ብዙ አልተቸገርንም።”
- ማሰታውቂያ -
“የአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ ከሆኑት የፋሲል እና የቡና አሰልጣኞች ጋር እየተነጋገርን ነው ያለነው።”
“የሴራሊዮን የወዳጅነት ጨዋታ ኢ.እ.ፌ ከስመጥር ስፖርት እና ኢንተርቴንመንት ጋር በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን፤ የኡጋንዳ ጨዋታ በኢ.እ.ፌ የተመቻቸ ነው።”
“የአፍሪካ ዋንጫ ድልድልን አስመልክቶ የትኛውም ምድብ ላይ ልንሆን እንችል ነበር በደረሰን ምድብ ላይ የተለየ ምለው ነገር የለኝም፤ በምድባችን የተለየ ነገር ለማሳየት እንሰራለን።”
©EFF