ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች !

የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር እና አመራር በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ታዛቢዎች የቀረቡለትን የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የጨዋታ ሪፖርቶች መርምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል ።

በሰባተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ አራት ጎሎች ከመረብ ሲያርፉ ካለፉት ሳምንታት ዝቅተኛው ሆኗል ።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አምበል እና የፊት መስመር አጥቂ ጌታነህ ከበደ በጅማ ዩኒቨርድቲ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ሀትሪክ የሰራ የመጀመሪያው ተጫዋች ሲሆን በሊጉ ሙጂብ ቃሲም እና ጌታነህ ከበደን በመከተል ሶስተኛው ተጫዋች ሆኗል ።

በሰባተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀያ አንድ ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 181 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በሰባተኛው ሳምንት ጨዋታዎች የቀይ ካርድ የተመለከተ ተጫዋች የለም ። ከታዩ ሀያ አንድ የማስጠንቀቂያ ካርዶች ውስጥ አስራ አራት የሚሆኑት ተጫዋቾች ባሳዩት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በመሆን ወይም በመጫወት ባሳዩት ድርጊት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ።

በሰባተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ 9.75 ነጥብ በማምጣት የዚህ ሳምንት ስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል ።

በሳምንቱ ከተላለፉ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መካከል :-

1. ጅማ አባጅፋር አርብ ጥር 7 2013 ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ ሰባተኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር አምስት ደቂቃ ዘግይቶ አንዲጀመር ምክንያት ስለመሆኑ ከጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ክለቡ ለፈፀመው ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት 15,000 ቅጣት እንዲከፍል፤ በተጨማሪም ጨዋታውን በብሮድካስት የሚያስተላልፈው ድርጅት ሼር ካምፓኒው ላይ የሚያስተላልፈው የገንዘብ ቅጣት ካለ ክለቡ ወጪውን ሙሉ በሙሉ እንዲከፍል ወስኗል።

2. ታከለ ጨቅሌ (የባህርዳር ከተማ ቡድን መሪ) ቅዳሜ ጥር 8 2013 ክለቡ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የሰበታኛ ሳምንት የ ጨዋታ መርሐ ግብር ካለቀ በኋላ የዕለቱን አራተኛ ዳኛ አፀያፊ ስድብ መሳደቡና ለድብድብ መጋበዙ ከዋና ዳኛውና ከጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦበታል። የቡድን መሪው ለፈፀመው ጥፋትም በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ስድስት ጨዋታ እንዲታገድ እና ተጨማሪ 5,000 ብር ቅጣት እንዲከፍል ወስኗል።

3. የአንድ ቡድን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች የሚወጣው ፕሮግራም ከ72 ስዓት ማነስ የለበትም የሚለውን የውድድር ደንብ ለማክበር ሲባል በስምንተኛ ሳምንት ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል ጥር 13 2013 ዕሮብ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የሰዓት ቅይይር ተደርጓል ። በዚህም ዕሮብ ጥር 12 2013 ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና 4:00 ሰዓት በ 9:00 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከ አዳማ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል ።

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር እና አመራር ስነስርዓት ኮሚቴ በማሳሰቢያው ሁለት ጉዳዮችን በጥብቅ አንስቷል ። እነዚህም :-

1. ጨዋታው በብሮድካስት የሚያስተላልፈው ድርጅት የተጫዋቾች አሰላለፍ እና የጨዋታ ፎርሜሽን ዘግይቶ እየሰረሰ በመሆኑ ስራችን ላይ ችግር እየፈጠረብን ነው የሚል ሪፖርት በማድረጋቸው ተጋጣሚ ክለቦች ስታዲየም እንደደረሱ በተሰጣቸው ፎርማት መሰረት ሙሉ መረጃ የያዘ አሰላለፍ እና የጨዋታ ፎርሜሽን ለጨዋታው ታዛቢ ወይም ለውድድር ስነስርዓት ኮሚቴ እንዲሰጡ አሳስቧል ።

2. ክለቦች ጨዋታ በሌላቸው ቀንና ሰዓት ከተፈቀደላቸው ሁለት የክለብ አመራሮች ውጪ ወደ ስታዲየም መግባት የማይችሉ መሆኑ ተገልጿል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor