በ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ጥሩ ተፎካካሪ የነበረዉ ሀድያ ሆሳዕና በዝዉዉር መስኮቱ ከተወሰኑ ነባር ተጫዋቾቹ ጋር መለያየቱ ይታወሳል። በተቃራኒዉ በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀላቸው ታዉቋል።
በዛሬዉ ዕለት የመጀመሪያ ፈራሚ በመሆን ወደ ክለቡ ያመራው የቀድሞዉ የሀላባ ከተማ ተጫዋች እና ያለፉትን ስድስት የዉድድር አመታት በቡናማዎቹ ቤት ወጥ በሆነ አቋም መጫዎት የቻለዉ ሁለገቡ ተጫዋች እያሱ ታምሩ መሆኑ ታዉቋል። ተጫዋቹ በዛሬዉ ዕለት ረዘም ላሉ አመታት ከቆየበት ኢትዮጵያ ቡና ጋር በመለያየት ወደ ሀድያ ሆሳዕና ማምራቱ ተረጋግጧል።
ሌላኛው ወደ ሀድያ ሆሳዕና ያመራዉ ደግሞ በትላንትናው ዕለት ከባህርዳር ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየዉ አማካዩ ሳምሶን ጥላሁን መሆኑ ታዉቋል። ከዚህ ቀደም ለደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ አማካዩ ያለፉትን ሁለት የዉድድር አመታት ከጣና ሞገዶቹ ጋር ቆይታ ካደረገ በኋላ የአንድ አመት ቀሪ ኮትራት እያለዉ ከክለቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ሀድያ ሆሳዕና ማምራቱ ዕርግጥ ሆኖአል።
አስተያየት ይስጡ