በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ ከወትሮ ለየት ባለ መልኩ በዝዉዉር ገበያው ላይ በንቃት በመሳተፍ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች አሁን ደግሞ በተቃራኒው ከግብ ጠባቂያቸዉ ዳንኤል ተሾመ ጋር መለያየታቸው ታዉቋል።
ከዚህ ቀደም ለሀምበሪቾ ዱራሜ እና አዲስአበባ ከተማ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ ግብ ጠባቂዉ የዉድድር አመቱን አዳማ ከተማን በአምበልነት እየመራ በጥሩ በቃት ካጠናቀቀ በኋላ በኋላ በዛሬዉ ዕለት በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ