ለ2014 ወደ ኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ለመግባት እየተደረገ ባለው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና መገባደጃው ላይ ደርሷል ።አስራ ስድስት ውስጥ የገባው ቦዲቲ ከነማ በቡሳ ከነማ በፍፁም ቅጣት ምት መሸነፉ ይታወሳል ።ሆኖም ግን ቦዲቲ ከነማ የተጫዋች ተገቢነት ክስ በቡሳ ከነማ ላይ መስርተዋል።
ለቡሳ ከነማ እየተጫወተ የሚገኘው ታደለ ላጫሞ በዘንድሮ ዓመት በአማራ ሊግ ለቡሬ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለመጫወት ውል ተፈራርሞ የተጫወተ ሲሆን የውል ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ለቡሳ ከነማ እየተጫወተ ይገኛል ።ቦዲቲ ከነማ እግር ኳስ ክለብም ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ክስ መስርተል ።ከጨዋታው በኋላም በደንቡ መሰረት አንድ ሺህ(1000) ብር በማሲያዝ ክሳቸውን አስገብተዋል።


ውድድሩን እየመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሀገር አቀፍ ክለቦች ሻምፒዮና የውድድርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ምላሽ ለመስጠት የኮሚቴውን መሟላት እየጠበቀ እንደሆንም አሳውቀውናል ።
መረጃውን ያደረሰን የቦዲቲ ከነማ ቡድን መሪ አቶ አሸናፊ አበራ ነው

አስተያየት ይስጡ