በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው የሀድያ ሆሳዕና ክለብ በ2013 የውድድር አመት ከተጫዋቾች ክፍያ ጋር በተያያዘ ብዙ ውዝግቦችን ማስተናገዱ ይታወሳል ። ከአምናው ስህተቱ የተማረ የማይመስለው ክለቡ የውድድር አመቱ ገና ከመጀመሩ ከተጫዋቾቹ ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብቷል ።
በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ከፋሲል ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ሰአታት በቀሩበት ጊዜ 12 ተጫዋቾች ከክለቡ ጋር የተስማማነውን የፊርማ ገንዘብ ሊያስገቡልን ፈቃደኛ አልሆኑም በማለት ጨዋታውን አናደርግም አሉ ። ነገር ግን በዋና አሰልጣኙ ሙሉጌታ ምህረት ተማፅኖ ጨዋታውን አድርገዉ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል ።
ከዚህ ጨዋታ በኋላ እነዚህ 12 ተጨዋቾች ከክለቡ ጋር ልምምድ መስራት ያቆሙ ሲሆን የክለቡ አመራሮች ክፍያውን የማይፈፅሙላቸው ከሆነ በነገው ዕለት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ያላቸውን ጨዋታ እንደማያደርጉ ተናግረዋል ።
አስተያየት ይስጡ