በጠቅላላ ጉባኤው ላይ አቶ ባህሩ ጥላሁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ፣ አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ወጣቶችን ስፖርት ዋና ሀላፊ እንዲሁም የተለያዮ በተገኙበት በኢትዮጵያ ሆቴል ተደረገ ።
በጉባኤው ላይ የአምስት ዓመት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን መህበሩ የተጣራ 13 ሚሊዮን ብር ሀብት እንዳለው የገለፁ ሲሆን አያይዘውም በለፉት አራት አመታት የስፖንሰር ገቢ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ገልፀዋል ።
በተጨማሪም ክለቡ ከ ስፖንሰር ድርጅች ያልተሰበሰበ 41 ሚሊዮን ብር መግለፅ ችሏል ።
በመጨረሻ ጉባኤው 10 የቦርድ ሀላፊዎችን መሾም የቻሉ ሲሆን አቶ አብነት ገ / መስቀል በድጋሚ መመረጥ ችሏል ።

- ማሰታውቂያ -
በዚህም መሰረት 1- አቶ አብነት ገ /መስቀል
2-አቶ መሀመድ አሊ
3-አቶ ንዋይ በየነ
4-አቶ ሳምሶን አቡዲሳ
5-አቶ ሚሊዮን አለሙ
6-አቶ አበባው ዘውዴ
7-አቶ ቅባቱ ወልደሰንበት
8- አቶ ሰለሞን እሸቱ
9-አቶ ወንዱ ለገሰ
10-ፍስሀ ሞላልኝ በመሆን መመረጥ ችሎዋል ።


