የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
- ግርማ ዲሳሳ (ባህርዳር ከተማ): የመታወቂያ ቁጥር አርብ ጥቅምት 14 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- መቻል ክለቡ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ባደረገው የ2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የመቻል ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ብሩክ ማርቆስ
- በረከት ደስታ
- ዓለምብርሀን ይግዛው
- ዳዊት ማሞ
- መሃመድ አበራ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
3. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡ በ2ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ ስላለመገኘቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ከለቡ በፈጸመው ጥፋት በፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 10 ተቁ 7 መሰረት ብር 5000/ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ሲዳማ ቡና ክለቡ በ2ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ ስላለመገኘቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ከለቡ በፈጸመው ጥፋት በፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 10 ተቂ 7 መሰረት ብር 5000/አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


