ፋሲል ከተማ ተጫዋች ለማስፈረም መስማማቱ ተገለፀ !

 

ያለፉትን ዓመታት በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻሉት ፋሲል ከተማዎች የፕርሚየር ሊጉን የዋንጫ ባለቤት ይሁን እንደሻው ለማስፈረም መስማማታቸው ተገልጿል ።

የዘንድሮውን የውድድር ዓመት በሀድያ ሆሳዕና ማሳለፍ የቻለው ይሁን በአፄዎቹ ቤት ቀጣዩን ዓመት እንደሚያሳልፍ ሲጠበቅ ለቡድን ትልቅ ግልጋሎትን እንደሚሰጥ ይጠበቃል ።

ይሁን እንደሻው በቀጣይ ዓመት በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ መሳተፉን ላረጋገጠው ፋሲል ከተማ የቡድን ስብስብ ተጨማሪ ግብዐት እንደሚሆን ይታመናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor