ዛሬ ቅዳሜ በኮንጎዋ ሉሙባሺ ከተማ በፓላንድ አስተናጋጅነት ለሚደረገው የ2026 ከ20 አመት በታች የሴቶች የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሜዳዋ ላይ አይቮሪኮስትን አስተናግዳ 1ለ0 ስታሸንፍ ኢትዮጵያዊያን የሀገራችን ዳኞች ጨዋታውን በብቃት በዳኝነት መርተውት በሰላም አጠናቀዋል።
በመሐል ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኛ ሲሳይ ራያ ፣ በረዳት ዳኝነት ደግሞ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ወይንሽት አበራ እና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ይልፋሸዋ አየለ ከሩዋንዳዊቷ አራተኛ ዳኛ ጋር በብቃት ጨዋታውን አመሻሹን መርተው አጠናቀዋል።
ባለፈው ሳምንት በሜዳዋ 2ለ0 የረታችው አይቮሪኮስት በድምር ውጤት 2ለ1 አሸንፋ ማለፏን አረጋግጣለች።



