ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዝውውር እንዳያደርግ ታገደ !

 

ከቀድሞ ተጨዋቹ ታፈሰ ተስፋዬ ጋር በገጠመው የፍትህ አደባባይ የተሸነፈው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለተጨዋቹ መክፈል ያለበትን ደመወዝ ባለመክፈሉ ዝውውር እንዳያደርግ ታገደ፡፡

የክለቡ የሴት ቡድን ተጨዋቾችን ለማስፈረም ወደ ፌዴሬሽኑ ያቀኑት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በፌዴሬሽኑ የፍትህ አካላት የተወሰነባቸውን የተጨዋቹን ቀሪ ደመወዝ እስኪከፍሉ ድረስ ምንም አይነት ዝውውር ማድረግ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል፡፡

በዚህ መሠሉ ችግር ውስጥ ያሉ ክለቦች የተወሰነውን መፈጸም ካልቻሉ ተመሳሳይ የክልከላ ርምጃ እንደሚወስድ ፌዴሬሽኑ ጠንካራ አቋም መያዙ ታውቋል፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport