ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋና ስራ አስኪያጁን አሰናበተ

ኢትዮ ኤሌክትሪክን በዋና ስራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ለማ ደበሌ እንዲነሱ ተወሰነ።
የስፖርት ክለቡ ቦርድ በወሰነው ውሳኔ መሰረት አቶ ለማን በማሰናበት በማስታወቂያ ቋሚ ስራ አስኪያጅ እስኪቀጠር ድረስም በጊዜያዊነት አቶ ሲሳይ ለማ ቦተውን ተክተው እንዲሰሩ መወሰኑን አስታውቋል።
ቦርዱ በላከውም ደብዳቤ ተሰናባቹ ስራ አስኪያጅ በስራቸው ያለውን ንብረቶች ለአዲሱ ስራ አስኪያጅ እንዲያስረክቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።

በክለቡ ውስጥ ይታዩ የነበሩት ድክመቶች እንዲሁም ወደ 14 ሚሊየን ብር በሚገመተው የማሊያ ግዢ ላይ ሊሰራ የነበረውን ደባ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ያከሸፈው ሀብታሙ መንገሻን ውሉ እንዳይታደስ ቦርዱን በማሳመን ትልቅ ሚና ተወጥተዋል በሚል የሚተቹት ተሰናባቹ ስራ አስኪያጅ ዘንድሮም የክለቡ ተጨዋቾች ትጥቅ ሳይሰጣቸው ለመቅረቱ እንደምክንያት ተጠርተው ተተችተዋል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport