ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ድቻን ከሰሰ…

በአሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነ ማርያም የሚሰለጥነው ወላይታ ድቻ ከድረሬዳዋ ከተማ ያስፈረመው ግብ ጠባቂው ወንደሰን አሸናፊ ዝውውር ክስ አምጥቶበታል።

ከድሬዳዋ ከተማ ታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ሰኔ 30/2014 ድረስ ውል ያለው ግብ ጠባቂው ከድሬዳዋ ጋር ያለውን ውል ሳያፈርስ ለወላይታ ድቻ መፈረሙ ድሬዳዋ ከተማን አስቆጥቷል። ይህን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በወላይታ ድቻ ፔጅ ላይና ሌሎች ድረገጾች ላይ ያለውን ዜና በመረጃነት በመያዝ ለፌዴሬሽኑ የክስ ደብዳቤ ማስገባታቸው ታውቋል።

ተጨዋቹ በበኩሉ አካሄዱ እንደማያወጣው በመረዳት ይመስላል ድሬዳዋ ከተማዎች ውሉን እንዲቀዱለት ቢማጸንም የድሬዳዋ ከተማ አመራሮች ግን በውሉ መሰረት የሚጠበቅበትን መልሶ ክለቡን መልቀቅ እንደሚችል በመግለጽ ወላይታ ድቻዎችን ውል መልቀቂያ ሳይጠይቁ ለምን እንዳስፈረሙት በመጠየቅ ክሳቸውን ለፌዴሬሽን አስገብተዋል።

ወንድወሰን አሸናፊ ወላይታ ድቻ የጥሎማለፍ ዋንጫ ሲያነሳ የክለቡ አባል እንደነበር ከክለቡ ፔጅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport