በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክለው ኢትዮጵያ ቡና ከነገ በስቲያ ከዑጋንዳው ገቢዎች ባለስልጣን ጋር
ለሚያደርገው ጨዋታ ዛሬ ምሽት ወደ ካምፓላ ያቀናል።
ቡናማዎቹ ከሀገር ውጪ በሚያደርጉት ጨዋታ ዋና አሰልጣኙ ካሳዬ አራጌ የካፍ ኤ ላይሰንስ ባለመያዛቸው ተጠባባቂ ቦታ ተቀምጠው ቡድናቸውን እንደማይመሩ ታውቋል።
ካፍ የሻምፒየንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ የሚካፈሉ ክለቦችን የሚመሩ አሰልጣኞች ኤ ላይሰንስ መያዝ አለባቸው የሚለው አስገዳጅ ህጉን ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ ሲሆን አሰልጣኝ ካሳዬ አሜሪካ ካገኙት ላይሰንስ ውጪ የካፍ ኤ ላይሰንስን ባለመያዛቸው ካፍ ቡድናቸውን ከማይመሩ 21 አሰልጣኞች መሃል መሆናቸውን አሳውቋል።
ከክለቡ አሰልጣኞች መሃል ኤ ላይሰንስ ያላቸው አሰልጣኝ ጸጋዘአብ አስግዶም በዋና አሰልጣኝነት ቡድናቸውን ሊመሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል።
በሻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ፋሲል ከነማዎች ባህርዳር ላይ ከነገ በስቲያ እሁድ የሱዳኑ አልሂላልን ሲያስተናግዱ ኤ ላይሰንስ በያዙት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እንደሚመሩ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ