ኢትዮጵያ ቡና አራት ተጨዋቾቹን ቀጥቷል

ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘ ኢትዮዽያ ቡና አራት ተጨዋቾቹ ላይ የደመወዝ ቅጣት አስተላለፈ።

ደብዳቤው ለአራቱም ተጨዋቾች ያልደረሰ ሲሆን ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ በቅርቡ የአራት አመት ኮንትራቱን ያደሰው ታፈሰ ሰለሞን፣ ሚኪያስ መኮንን፣ አዲስ ፍሰሃና ሃይሌ ገ/ትንሳኤ ባህርዳር ላይ ባሳዩት የዲሲፕሊን ጥሰት የደመወዝ ቅነሳ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

ይህ የኢትዮዽያ ቡና ቅጣት ከቅዱስ ጊዮርጊስ በመቀጠል ሁለተኛው ክለብ አድርጎታል። በድሬዳዋ ከተማ መዝናናት ያበዙ የክለቦቻቸው ህግን የጣሱ ተጨዋቾች በርካቶች በመሆናቸው ሌሎች ክለቦችም ተመሳሳይ ርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport