የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ጋር የአጋርነት የውል ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ጋር ሕክምናን በተመለከተ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ወሎ ሰፈር በሚገኘው ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራርሟል፡፡

በኘሮግራሙ መክፈቻ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራ በሰጡት አስተያየት “ይህ ስምምነት የስፖርቱን አቅም ለመገንባት የሚያስችል ዝግጅት በመሆኑ ደስተኛ ነኝ።
ስምምነቱ በቀላሉ የተገኘ ሳይሆን ሰፊ ስራ የተሰራበት ሲሆን የሕክምና ባለሙያ ቅጥር በማከናወን  በፌዴሬሽኑ የሚዘጋጁ ወደ ሰባት የሚጠጉ ውድድሮች እነዚህም በዋናው ቡድኖች በወንዶችና በሴቶች ፣ በከፍተኛ ሊግ ፣ በአንደኛ ሊግ፣ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች እንዲሁም ከ100 በላይ ለሚሆኑ የፌዴሬሽኑ ሠራተኞች የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እድሉን ይፈጥራል፡፡ በተመሳሳይ የውዳሴ ዲያግኖስቲግ ማዕከል በብሔራዊ ቡድኖች ትጥቆችና በተለያዩ የስታዲየሞች ዝግጅትና የተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች ላይ ማዕከሉን የሚያስተዋውቅበት እድል የሚያገኝ ሲሆን ከገንዘብ አኳያ ሲታይ ፌዴሬሽኑን የተሻለ ተጠቃሚ የሚያደርገንን እድል የፈጠረ በመሆኑ እጅጉን ደስተኛ ነኝ” በማለት ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕክምና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ  በበኩላቸው “ እስከ አሁን ድረስ የፌዴሬሽኑ የሕክምና እንቅስቃሴ በሕክምና ኮሚቴ እየተመራ የቆየ ሲሆን አሁን በሕክምና ዲፖርትመንት ለማቋቋም ጅማሮ ላይ እንገኛለን፡፡ በቀጣይ ምን መሆን አለበት? ምንስ ላይ መሰራት ይኖርበታል በሚል ብሔራዊ ቡድኖችን መሠረት አድርገን ሌሎችንም የውድድሮች አካላት ተጠቃሚ ለማድረግ በአጋርነቱ ቀጣይነት ላይ እንሰራለን፡፡ ለእዚህም ከስምምነቱ በፊት የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል በቅርቡ ለበርካታ ብሔራዊ ቡድኖችና እና ለፌዴሬሽኑ ባለሙያዎች በነፃ የኮቪድ ምርመራ በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡” በማለት አስረድተዋል፡፡

የውዳሴ ዲያግኖስቲክ   ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር  የሆኑት አቶ ዳዊት ኃይሉ በእለቱ በሰጡት አስተያየት “ እንዲህ አይነት የኢትዮጵያን ባንዲራ በያዘው ሥራ ላይ አጋር መሆን ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው ብለን እናምናለን፡፡ ውዳሴ ብቻ በአገሪቱ ላይ ያሉውን  የህክምና ክፍተት ለመሙላት አይችልም ፡፡ ጉልበት ያለው በጉልበቱ ፣ እውቀት ያለው በእውቀቱ በማገዝ ነው፡፡

እንዲሁም በቅርቡ ዋሊያዎቹ ያሰሙን ተስፋ መልካም ነው፡፡ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ እንኳን ደስ ያለን፡፡ በማለት የደስታ መልዕክት በማስተላለፍ አክለውም ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ከ12 ዓመታት ጀምሮ እየሰራ የሚገኘው  በርካታ ሥራ ሲሆን ከእንደዚህ ዓይነት ተቋማት ጋር በአጋርነት መስራት አንዱ ዓላማው ነው፡፡ ይህ ጅማሮ ለሌሎችም መነሳሳት ሲሆን ስምምነቱ ጤናቸው ሲታወክ ብቻ ሳይሆን ጤናማም ሆነው ክትትል የሚያደርጉበት ከእዛም ባለፈ ምክክር እና ጥምረት የሚፈጠርበት ነው፡፡ በቀጣይም ማዕከሉ በሚከፍታቸው የጤና አገልግሎቶች ተጠቃሚነቱ የሚከናወን ይሆናል፡፡ በዚህም ትልቅ ኩራት የተሰማኝ በመሆኑ በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ ነን “ በማለት አስረድተዋል።

Source- EFF

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team