ኢትዮጵያ ቡና የክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጀመሪያ ፈራሚውን ይፋ አድርጓል።
የክለቡ ቀዳሚ ፈራሚ የሆነው ዘላለም አባተ ሲሆን በቡናማዎቹ ቤት ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።
ዘላለም አባተ ያለፉትን ተከታታይ አምስት አመታት በጦና ንቦቹ አሳልፏል።
ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 21 የሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 3 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን ፋሲል ከነማ ከራሱ የሜዳ ክፍል መቶ ያስቆጠረው ግብ እጅግ አስደናቂ እንደነበር ይታወሳል።
- ማሰታውቂያ -


