አክስዮን ማህበሩ አስቸኳይ ጉባኤውን በካፒታል ሆቴል ያደረገ ሲሆን በ 4ኛው እና 5ኛው መደበኛ ጉባኤ የተወሰዱ ቪዲዮ ለክለብ ተሳታፊዎች ማቅርብ ችለዋል
በዛሬው ጉባኤ ላይ ሁለት አጀንዳዎች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያ አጀንዳ የነበረው የክለቦች ክፍያ አስተዳደር መመሪያ ማሻሻያ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል በተጨማሪም በጉባኤው የቀረበው ሀሳብ ገንቢው ተወስዶ ለማማሻሻል ተወስኗል ። ሁለተኛ አጀንዳ የነበረው የክለቦች የክፍያ ጣሪያ በአክስዮን የቀረበ ሲሆን ከ 2018-2020 ዓ.ም አማራጭ የቀረበ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጥቅል ክፍያ ጣሪያ ጉባኤው በመወያያት በ ቀጣይ የክፍያ ጣሪያ 70,000,000.00 እንዲሆን ተወስኗል ።
በጉባኤ ላይ የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ : መቶ ሀለቃ ፍቃደ ማሞ እና የቡድን አመራሮች መገኘት ችለዋል።



