ከቡናማዎቹ ጋር ልምምድ እየሰራ የሚገኘው የግብ ዘቡ ክለቡን በይፋ ሊቀላቀል ተቃርቧል።
በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ስልጠናውን ከጨረሰ በኋላ በሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ውስጥ በመጫወት ከ17 እና ከ20 አመት በታች ቡድኑን አገልግሏል። ወደ ዲላ ከተማ በመሐል አምርቶ በከፍተኛ ሊጉ ላይ ከተጫወተ በኋላም በድጋሚ ወደ ሀዋሳ ከተማ ተመልሶም የመጫወት ዕድልም ነበረው።
በሀዋሳ በነበረው ሁለት የውድድር ዘመናት ባሳየው ብቃት ወደ መቻል በማምራትም ጭምር ቆይታን ያደረገው ወጣቱ የግብ ዘብ ዳግም ተፈራ (ቻቺ) አዳማ ከተማን ሦስተኛው የፕሪምየር ሊግ ክለቡ በማድረግ ያሳለፈ ሲሆን ከቀድሞው ግብ ጠባቂ በረከት አማረ ጋር ንግግር ቢያደርግም ዳግም ተፈራን ምርጫው በማድረጉ ግብ ጠባቂው ከክለቡ ጋር ልምምድ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በሰዓታት ውስጥም በይፋ ለኢትዮጵያ ቡና ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።


