ከቀናት በፊት የነገርናችሁ ሙከራ ላይ የነበረው ተከላካይ ለአዞዎቹ በይፋ ፈረመ
ከቀናት በፊት እንዳስነበብናችሁ አርባምንጭ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም የሙከራ ዕድል መስጠቱን ነግሬያችሁ ነበር ፣ በዚህም መሠረት አጥቂው ፍቃዱ አለሙን ትላንት ያስፈረመው ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ተከላካዩ አማረ በቀለን በልምምድ ባሳየው አቋም የግላቸው አድርገዋል።
የቀድሞው የድሬዳዋ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ላለፉት ስድስት ወራት በአቃቂ ቃሊቲ የነበረው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አማረ በቀለ እስከ አመቱ መጨረሻ ነው ለአዞዎቹ መፈረም የቻለው።



