ወደ አርባምንጭ ከተማ ሊያመሩ ከጫፍ ደርሰው የነበሩት አሰልጣኝ መዳረሻው ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።
በያዝነው የውድድር ዘመን በፕሪምየር ሊጉ ባስመዘገው ውጤት የተነሳ አሰልጣኝ አብይ ካሳሁን ራሱ ባስገባው መልቀቂያ ለመለያየት የበቃው ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል ለመቅጠር ጥረት ቢያደርግም የዩጋንዳው ክለብ ኮንትራት አለው አለቅም ማለቱን ተከትሎ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን ምርጫው በማድረግ በሁለት አመት ውል መሾማቸውን አሰልጣኙ በስልክ አረጋግጠውልኛል።
የቀድሞው የሐረር ቢራ ፣ ስሑል ፣ ሽረ እና ድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ያለ ስራ ቢያሳልፉም ከቀናት በፊት ወደ አርባምንጭ ከተማ ሊያመሩ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻም ማረፊያቸው ኢትዮጵያ ቡና በሁለት አመት ውል ሆኗል።



