መነሻ ገጽ አትሌቲክስ በመጪው እሁድ ለሚካሄደው 39ኛው የጃን-ሜዳ እና የ1ኛው የምስራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር መግለጫ ተሰጥቷል
አትሌቲክስዜናዎችየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

በመጪው እሁድ ለሚካሄደው 39ኛው የጃን-ሜዳ እና የ1ኛው የምስራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር መግለጫ ተሰጥቷል

አጋራ
አጋራ

ዓላማውን ክልሎችን ከተማ አስተዳደሮችን ክለቦችን እና የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት በአለምአቀፈሰ ሀገር አቋራጭ ውድድር በማሳተፍና ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ ፣ ለአትሌቶች የውድድር እድል በሀገር ውስጥ ለመፍጠር እና አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታታት ያደረገው የጃን ሜዳ የሀገር አቋራጭ ውድድር ዘንድሮ ለየት ባለ መልኩ ከመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ሀገር አቋራጭ ሻምፕዮና ጋር በአንድ ላይ የፊታችን ዕሁድ የካቲት 6 ቀን በጃንሜዳ የሚደረግ ይሆናል ።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከውድድሩ ጋር ተያይዘው ያሉ ጉዳዮች በፌዴሬሽን የተለያዩ ሀላፊዎች ቀርበዋል ። በቅድሚያ ንግግር በማድረግ መግለጫውን የከፈቱት የቀድሞው የማራቶን አትሌት እና በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ገዛኸኝ አበራ ሲሆኑ በመቀጠልም የፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዮሐንስ እንግዳ ስለውድድሩ ቅድመ ዝግጅት እና በውድድሩ ዕለት ስለሚኖሩ ሁነቶች ፤ የተሳትፎና እና ውድድር ባለሙያ የሆኑት አቶ አስፋው ዳኜ ከተሳታፊ አትሌቶች እና የሽልማት መጠን ፤ አቶ አሸብር ደምሴ የተሳትፎና የውድድር ስራ ሂደት መሪ ውድድሩ ስለሚካሄደበት ስፍራ እና ሩጫው የሚሄድበትን ርቀት በበስዕላዊ መረጃ በማስደገፍ ያብራሩ ሲሆን ከህክምና እና በውድድሩ ከኮቪድ ፕሮቶኮል ጋር በተያያዝ ስለተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ዶክተር በዛብህ ወልዴ እንዲሁም በዕለቱ ከዲያስፖራ ሽኝት ጋር በተያያዘ ከውድድሩ ጎን ለጎን በሚኖረው መርሀ ግብር ዙሪያ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር የማህበረሰብ ተሳትፎ ስራ ሂደት መሪ በሆኑት አቶ ተስፋዬ በቀለ አማካኝነት ገለፃዎች ተደርገዋል ።

የፊታችን ዕሁድ በሚካሄደው ውድድር ላይ ለዘጠኝ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ግብዣ የተደረገ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አምስቱ ( ኬንያ ፣ ኤርትራ ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ታንዛንያ ) ለመሳተፋቸው ማረጋገጫ ሰጥተዋል ። እንዲሁም ከሀገር ውስጥ 5 ክልልሎች ሁለት የከተማ አስተዳደሮች 19 ክለቦች እና ተቋማት 55 ቬትራን እና 111 የግል ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ።

በዕለቱ የሚካሄዱት ውድድሮች በ5 የተከፋፈሉ ሲሆኑ በ6 ኪ.ሜ ወጣት ሴቶች ፣ በ10 ኪ.ሜ አዋቂ ሴቶች ፣ በ8 ኪ.ሜ ወጣት ወንዶች ፣ በ10 ኪ.ሜ አዋቂ ወንዶች እና በ8 ኪ.ሜ ድብልቅ ናቸው ። በአጠቃላይ በሀገር አቋራጭ ውድድሩ ላይ 473 ወንዶች እና 251 ሴቶች በድምሩ 724 አትሌቶች ይሳተፋሉ ።

ሌላው በመግለጫው የተነሳው ለአሸናፊ አትሌቶች የሚሰጠው የገንዘብ መጥን ሲሆን ከዚህ ቀደም ከነበሩት የጃን ሜዳ ሀገር አቋራጭ ውድድሮች ማሻሻያ የተደረገበት ሲሆን በአጠቃላይ ከ840,000 ብር በላይ በሽልማት መልክ ተዘጋጅቷል ።

አትሌቶች ከውድድሩ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከኮቪድ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምርመራ ውጤት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከተወዳዳሪዎቹ በተጨማሪም ውድድሩን ለመመልከት በጃን ሜዳ የሚታደሙ የአትሌቲክስ አፍቃሪዎች የኮቪድ 19 መከላከያዎችን በአግባቡ በመጠቀም ውድድሩን እንዲመለከቱ ዶክተር በዛብህ ወልዴ በአፅንኦት ተናግረዋል ። በመጨረሻም ጥቂት ጥያቄዎች ቀርበው መልስ ከተሰጠባቸው በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫው ተጠናቋል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...