በ ልደታ ክ/ከተማ ክፍለ ከተማ ማራኪ እንቅስቃሴ ማሳየት የቻለው እና በ ዘንድሮ የውድድር ዘመን በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመያዝ ማራኪ እንቅስቃሴ እና ሊጉን በመመራት ላይ የሚገኘው አሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ የሀትሪክ ስፖርት እንግዳ በመሆን ቀርባል ።
ሀትሪክ :- ኮች ኤርሚያስ ወደ እግር ኳስ እንዴት ሊመጣ ቻለ ?
ኤርሚያስ :- እንደ ማንኛውም ልጅ በሰፈር ውስጥ እና በትምህርት ቤት የመጫወት እድል ሳገኝ ያኔ ፍቅሩ አደረብኝ ወደ እግር ኳስ መጣው
ሀትሪክ :- ከሴቶቹ በፊት ወንዶች የማስልጠን አጋጣሚአጊኝተህ ነበር ?? እነማንን ?
- ማሰታውቂያ -
ኤርሚያስ :- ማሰልጠን ጀመርኩት ወንዶችን ነው ያው ስጀምር ፕሮጀክት ላይ U13 ነው ያሰለጠንኩት በመቀጠል ወንድ ቡድን U15 እና U17 አልታ ፊያ የሚባል የእስፔን ቡድን ነው ያሰለጠንኩት በመቀጠል ጃልሜዳ ትህምህርትና ስልጠና ማህከል ታዳጊዋችን ለረጅም ጊዜ !
ሀትሪክ :- በአሰልጣኝነት በወረቀት ደረጃ የምን ላይሰንስ አለክ ?
ኤርሚያስ :- የB ላይሰንስና የእንግሊዝ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ ሌብል 1 ሌብል 2 ሌብል 3 ወስጃለሁ በተጨማሪም የተለያዮ ስልጠናወችን ወስጃለሁ
ሀትሪክ :- በንግድ ባንክ ቤት የነበረህን ቆይታ ግለፀው ብትባል እንዴት ልትገልፀው ትችላለህ
ኤርሚያስ :- በንግድ ባንክ የነበረኝ ቆይታ እጅጉን ጥሩ ነበር ምክንያቱም ፈልገህ ተማምነህ የምሰራበት ቤት ነው ለዚህም አሰልጣኝ ብርሀኑ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል እኔ እራሴን በደንብ ያበቃሁበት እና ልምድ የወሰድኩበት ስለሆነ መቼም አረሳውም ለኔ መልካም ቤት ነው

ሀትሪክ :- በዋና አሰልጣኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ መያዝ የቻልከው ልደታን ነበር በልደታ የነበረህ ቆይታ ስኬታማ ነው ብለህ ታስባለህ ? በምን በምን መንገድ
ኤርሚያስ :- አዋ በልደታ ጥሩ ቆይታ ነበረኝ ምክንያቱም ያለኝን አቅም በደንብ እዳወጣ እድሉን ያገኘሁበት ክለብ ነበር ያለኝን አቅም በደንብ አውጥቼበታለሁ ይህንን ስል በምክንያት ነው ብዙ አመት በረዳትነት ነበር የሰራሁት በረዳትነት ስሰራ እንደሌሎቹ መሰርሰር ሳይሆን መማርን ነበር ያስቀደምኩት ስለዚህ መማር ጥቅሙ ደሞ ይህ ነው የተማርከውን አውጥተ መጠቀም ይህ ነው ውጤታማነት
ሀትሪክ :- ዘንድሮ ከዚህ በፊት በምክትል አሰልጣኝነት የሰራህበት ኢትዮ ኤሌትሪክ መተሀል ምን አይነት ስሜት አለው
ኤርሚያስ :- በጣም ልዩ ስሜት ነው የሚኖረው ምክንያቱም ምክትል በሆንክበት ቤት ዋና ሆነ መሾም ምን ያክል እንደሚያስደስት ቀላል አይደለም በጣም ደስተኛ ነኝ
ሀትሪክ :- ኮች ምን አይነት አጨዋወወት ይመርጣል ማለትም በፎርሜሽን በንወስድ የቱ ፎርሜሽን ኮች ኤርምያስን ይወክላል
ኤርሚያስ :- እኔ ኳስን መሰረት አድርጎ የሚያጠቃ ቡድን መገንባት ነው በኢንፎርሜስን ደረጃ 4 3 3 እና 4 2 1 3 እነዚህ ኢፎርሜሽን ይመቸኛል
ሀትሪክ :- በአሰልጣኝነት ዘመንህ በታክቲክ ይበልጠኝ የምትለው አሰልጣኝ
ኤርሚያስ :- በዚህ ደረጃ ማንም አይበልጠኝም
ሀትሪክ :- በአሰልጣኝነት ዘመንህ ካየሀቸው ሴት ተጨዋቾች የትኛው በአንተ ምርጥ ናት ወይም ታደንቃታለህ ።
ኤርሚያስ :- ወይ ሁለት ናቸው ሎዛ አበራ እና አረጋሽ ካልሳ
ሀትሪክ :- አሁን ወደ አስገዳጅ ጥያቄ ልጠይቅህ አጥቂ ናቸው ሶስቱም ነገር ግን አንዷን ነው መምረጥ ምትችለው :- ሎዛ አበራ : ረሂማ ዘርጋው ወይስ ሴናፍ ዋቁዋ ??
ኤርሚያስ :- ሎዛ አበራ
ሀትሪክ :- የኤርሚያስ ምርጥ የምንግዜም 11 እነማን ናቸው ??
ኤርምያስ :-
- በረኛ :- ታሪኳ በርገነ
ተከላካይ :-ቤቴሌሄም (ቶንቦ) ቅድስት ዘለቀ ታሪኳ ደቤሶ ቡዛየሁ ታደሰ
መሀል: ዙፋን ደፈርሻ ቤቴሊሄም መንተሎ ግራ መሳይ ተመስገን
አጥቂ :- ሎዛ አበራ፣ ዳግማዊት ፣አረጋሽ ካልሳ ናቸው ::
ሀትሪክ :- አሰልጣኝ ባትሆን ምን ትሆን ነበር ?
ኤርሚያስ :- የአውሮፕላን ቴክኒሻል የምሆን ይመስለኛል

ሀትሪክ :- የሴት ቡድን ማሰልጠን ፈተናዎች አሉት ይባላል ኮች ምን ትላለህ ?
ኤርሚያስ :- ፈተና በትኛውም የስራ መስክ የማይቀር ነው ነገር ግን ያን ያክል አይደለም ለሞያህ ታማኝ ከሆንክ ፈተና የለውም ካልሆንክ ግን ከባድ ፈተና ላይ ትወድቃለህ ለምሳሌ ወንድ ሴትን ሰርጀሪ ያደርጋል ሴት ደግሞ ወንድን ሞያ ስለሆነ ሁለቱም እኩል ነው ለሞያህ ካልታመንክ ግን ከባድ ነው ለኔ ፈተና አይደለም
ሀትሪክ :- ጀግኒት ካፕ በሚል በዘንድሮ የውድድር ዓመት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች አድርጋችዋል ውድድሩን እንዴት አየከው
ኤርሚያስ :- ውድድሩ እጅጉን በጣም ጥቅም ያለውና ትርጉም ያለው ነው ምክንያቱም አንደኛ የሴቶች ጀግና እንደሆኑ እና እንደሚችሉ የሚያሳዩበት ትርጉም ያለው መሆኑ ስያሜው ሁለተኛው ደግሞ እንደ ቡድን ወይም እንደ ክለብ ከቅድመ ዝግጅት በሀላ ጨዋታ ለማግኘት እጅጉን እንቸገር ነበር ለዛም ትልቁን ችግሮች የቀረፈልን እና እራሳችንን ከጨዋታ ጨዋታ እንዴት ማረም እንዳለብን ያሳየን ትልቁ ስህላችን ነው የጀግኒት ውድድር እኔ በዚህ መልክ ነው የማየው
ሀትሪክ :- የ2018 ዓ.ም ውድድር ተጀምሯል ሶስት ሳምንት ከተደረገ በዋላ ሉሲዎቹ ጨዋታ ተቋርጧል አንተ የምትመራው ኢትዮ ኤሌትሪክ ደግሞ ሶስቱን ጨዋታ በማሸነፍ እየመራ ይገኛል እንደ አሰልጣኝ ዘንድሮ ምን እንጠብቅ ???
ኤርሚያስ :- እውነት ነው በአንደኝነት ውድድራችንን አጠናቀናል የሶስት ሳምንቱን እንደ እቅድ በ2018 የዋንጫ አቅደናል ከፈጣሪ ጋር ።
ሀትሪክ :- በመጨረሻም ማመስገን ምትፈልገው ካለህ
ኤርሚያስ :- በመጀመሪያ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ በመቀጠል ይህንን አሪፍ ቃለመጠይቅ ስላረክልኝ አንተን አመሰግናለሁ ሌላው ለኔ ውጤታማ እንድሆን ለሚመኙ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ።
እኛም እንደ ሀትሪክ ስፖርት ከልብ እናመሰግናለን መልካም የውድድር ዘመን እያልን በቀጣይ ሌላ እንግዳ ይዘን እስክንመለስ መልካም ጊዜ ተመኘን !!


