* …ውድድሩ የሚካሄድባቸው ከተሞችም ታውቀዋል
*…ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ ክትባት
ተጠይቋል…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ
ከጨዋታ በፊት ያለውን ክትባት ለማስቀረት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘውን ክትባት ለመውሰድ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን መጠየቁን ገልጿል።
ይሄ ክትባት የሚሰጠው አንዴ በመሆኑ ከጊዜ ጋር ጥቅም ስላለው የቡድን አባላት የውድድር መሪዎች እንዲወስዱ መጠየቁ ተነግሯል።
በ2013 በታየው የፍትህ ክፍተትን ለማስተካከል ጠንክሮ እየሰራ ሲሆን በተለይ ዘንድሮ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ተወካይ በአዲስ አበባና በጅማ ከተማ ውድድሮች ላይ ሳይገኝ ከባህርዳር ጀምሮ የመገኘቱ ክፍተት በ2014 እንደማይከሰት አመራሮቹ አስረድተዋል። ከሜዳ ጋር ተያይዞ ውድድሩ የሚካሄድባቸው ሜዳዎች መመዘኛውን ካላሟላ በፍጹም ውድድር እንደማይደረግ አስታውቋል። ከዳኝነት ጋር ተያይዞ ምደባውን ከፐርፎርማንስ ጋር ተያይዞ ምደባ እንደሚደረግና ከፌዴሬሽኑ ዳኛ ኮሚቴ ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልጿል። ከዚህም ውጪ በመጪው መስከረም ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አሰልጣኞች ስልጠና ይሰጣል ተባለ።
የሊግ ካምፓኒውሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ እንደተናገሩት “ከሆላንድ በሚመጡ ባለሙያዎችስልጠና ስለሚሰጥ በወቅቱ አሰልጣኞቻችሁን እንድትልኩ እጠይቃለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።
መቶ አለቃ ፈቃደ በቅሬታ መልክ የገለጹት “ወደየክለቦቹ ስንደውል አይነሳም ወደ ግል ስልክ ብንደውል አታነሱም ይህን አስተካክሉ የሊጋችንን ጥራት የሚያሳድጉ ጥናቶች እየተደረጉ በመሆናቸው ለመጨረሻ ውሳኔ የናንተ ግብአት ያስፈልጋልና ሲደወልላችሁ አንሱ” ሲሉ አሳስበዋል።
ውድድሮቹ የሚካሄዱበት እስታዲየሞችም ይፋ ሆነዋል በዚሁ መሠረት ሐዋሳ ከተማ ፤ አዳማ ከተማ ፤ ድሬዳዋ ከተማ ፤ ጅማ ከተማ ፤ ባህርዳር ከተማ እናአዲስአበባ የ2014 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን እንደሚያዘጋጁ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ