በአቤኔዘር አበበ
የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ፦ የግብ ድርቅና የእንግዳ ቡድኖች የበላይነት በመክፈቻው ሳምንት!

የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት በ9 ጨዋታዎች 11 ግቦች ብቻ በመመዝገብ ተጠናቋል። ጨዋታዎቹ በ5 ስታዲየሞች ሲካሄዱ፣ 8 ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ቀርተዋል፤ 11 ግቦቹንም 11 የተለያዩ ተጫዋቾች አስቆጥረዋል።
ከተካሄዱት ዘጠኝ ጨዋታዎች ሦስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ፣ በቀሩት ስድስት ፍልሚያዎች የሜዳ ባለቤቶች ተሸንፈዋል። ከዘጠኙ የሜዳ ባለቤቶች ሁለቱ ብቻ ግብ ማስቆጠራቸውም የግብ ምርታማነቱ ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል።
የሜዳ ጥቅም ድልን እንደማያረጋግጥ ባሳየው በዚህ ሳምንት፣ እንግዳ ቡድኖች በተረጋጋ አጨዋወትና በታክቲክ ዲሲፕሊን ውጤታማ ሲሆኑ፣ የሜዳ ባለቤቶች በደጋፊዎቻቸው ፊት የማሸነፍ ጫናን መቋቋም ተስኗቸዋል። በተጨማሪም ሁሉም ባለ መዳሊያ ክለቦች ድል ማድረግ አለመቻላቸው የውድድሩን ፉክክር ከጅማሮው አጠናክሮታል።
የሁለተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ሲጀምሩ፣ ትኩረቱ የግብ ድርቁን ማን ይሰብራል፣ የሜዳ ባለቤቶችስ ወደ ድል ይመለሳሉ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ