የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ያስተላለፈውን ቅጣት ተከትሎ ገንዘብ ያልመለሱ ተጫዋቾች ክለቦቻቸውን የማገልገላቸው ጉዳይ አጠራጥሯል።
የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ነገ አዲስ አበባ እና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየሞች ላይ በሚደረጉ አራት መርሀግብሮች ይጀመራሉ። በነገው ዕለትም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከ ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ ከሀዋሳ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ሲሆን በ2017 የውድድር ዘመን በሦስተኛ ወገን የገንዘብ ክፍያን ወስደዋል ተብለው በፋይናንስ ተቆጣጣሪ ኮሚቴው ዕገዳ እና የገንዘብ መልሱ ውሳኔዎች የተላለፈባቸው የሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ተጫዋቾች በነገው ጨዋታ ላይ የመሰለፋቸው ጉዳይ ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሜዳ ገብተው ቡድኖቻቸውን ላያገለግሉ እንደሚቸሉ ሀትሪክ ስፖርት መረጃውን ሰምታለች።
በሲዳማ ቡና በኩል አምበሉን ያሬድ ባዬን ጨምሮ ሀብታሙ ታደሠ ፣ መስፍን ታፈሠ ፣ ፍራኦል መንግስቱ ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ እና ደስታ ደሙ በሀዋሳ ከተማ በኩል ደግሞ አጥቂው እስራኤል እሸቱ እንዲሁም ከነገ በስቲያ ዕሁድ ከወላይታ ድቻ ጋር ጨዋታ ያለበት እና ከተቀጡ ሰባት ተጫዋቾች መካከል በአሁኑ ሰዓት በቡድኑ ውስጥ የተቀጡ ተጫዋቾችን የያዘው መቻል እንደ ዳዊት ማሞ ፣ ፍሪምፓንግ ሜንሱ ፣ አማኑኤል ዮሐንስ ፣ በረከት ደስታ እና ነስረዲን ሐይሉን በዚህ ውሳኔ መነሻነት ላይጠቀሟቸው እንደሚችሉ ተሰምቷል።
ይሁን እንጂ ተጫዋቾቹ ቅጣቸውን በአፋጣኝ የሚፈፅሙ ከሆነ ግልጋሎት ሊሰጡ እንደሚቸሉም ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -



