By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ከአሪፍ ፔይ ጋር የአጋርነት ስምምነት አደረገ
Share
Notification Show More
Latest News
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎች

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ከአሪፍ ፔይ ጋር የአጋርነት ስምምነት አደረገ

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 11 months ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ክለቦችን ለመደገፍ ያለመ ነው ያለውን የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምንት ከአሪፍ ፔይ ጋር አድርጓል።

በአዲስ አበባ ስታድየም በተካሄደው የአጋርነት ስምምነት መርሐግብር የአሪፍ ፔይ የቢዝነስ ዴቬሎፕመንት እና የፓርትነርሺፕ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ጌታቸው እና የደጋፊዎች ማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ደነቀው በሪሁን ፈርመዋል።

ስምምነቱ የክለብ ደጋፊዎች ምዝገባ ፣ የትኬት ሽያጭ ፣ የማልያ ሽያጭ የመሳሰሉትን እና ሌሎች የገንዘብ ዝውውሮችን በቀለለ እና በዲጂታል መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ነው ተብሏል።

ይህ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ የትንሳኤው መሰረት ነው ብለን እናስባለን ሲሉ የተናገሩት አቶ ግሩም ጌታቸው ናቸው።

- ማሰታውቂያ -

አክለውም ክለቦች አሁን ላይ እየሄዱበት ካለው መንገድ ጋር የጥቅም ግጭት አያመጣም ፤ አሪፍ ፔይ ከባንኮች ጋር በጋራ ይሰራል ገንዘቡ በአንድ መንገድ ተሰብሰቦ ክለቡ በመረጠው የባንክ አካውንት ገንዘቡ ይገባል ብለዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ እግር ኳስ እንወዳለን። ግን ዕድገት እያመጣ አይደለም እንደውም ወደ ቁልቁለት እነተጓዘ ነው። እንደ ተቋም እግር ኳሱን መደገፍ አላማችን ነው።”

“ይሄንን እግር ኳስ ዲጂታላይዝ ማድረግ ከቻልን የምንጠብቀውን ክለቦች ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ እንችላለን። ደጋፊ አላቸው ነገር ግን ከደጋፊዎቻቸው ገንዘብ የሚሰበስቡበት መሳሪያ የላቸውም።”

“ይህን መሳሪያ ከደጋፊ ማህበር ጋር ተዋህደን ሲስተም ፈጥረን እና አዘጋጅተን የክፍያ መንገዱን ማሳለጥ እስከቻልን ድረስ ክለቦች ራሳቸውን መቻል ይችላሉ የሚል ሀሳብ በመያዝ ብሎም ደግሞ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ብሎም ደግሞ ክለቦችን ለመደገፍ ነው ፤ ይህንን የአጋርነት ስምምነት ያደረግነው።”

እግር ኳስ ካለ ፋይናንስ ምንም ነው ያሉት አቶ ደነቀው በሪሁን በበኩላቸው እንደ ደጋፊ ክለቦች ገንዘብ የሚያገኙበት መንገድ ማመቻቸት አለብን የስምምነቱ ዋና አላማም ይህ ነው ብለዋል።

“ደጋፊ ማለት ምን ማለት ነው ክለቡን የሚደግፍ ማለት ነው። አብዛኞቻችን አሁን ያለንበት ሁኔታ ግን ከክለቡ ነው የምንደግፈው እና ስለዚህ የደጋፊዎች ጥምረት ዓላማው የተቋቋመበት ደጋፊ ማህበራትን በተለያየ መልኩ ማጠናከር ነው።”

“ስለዚህ ከዚህ ደግሞ ደጋፊ ማህበራት በቀላሉ ገንዘብ አምንጭተው ለክለቦቻቸው ገንዘብ የሚሰጡበት መልኩን ፕላትፎርም ማዘጋጀት አለብን ብለን ጥምረቱ ባስለማው ለደጋፊ ማህበራት በነፃ የሚሰጥ አሪፍ ፔይን እና ከጀርባው የዴሊቨሪ አገልግሎት ያለው መተግበሪያ ሰርተን ነው ወደዚህ ስራ የመጣነው። ይሄ ለደጋፊ ማህበራት በሙሉ በነፃ የሚሰጥ ነው”

ይህ ስምምነት በክለቦች የተመዘገቡ ደጋፊዎችን ቁጥር በማሳወቅ እና በመጨመር ለሌሎች አጋር ስፖንሰሮችም ጭምር ዳታዎችን ማቅረብ የሚቻልበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

“ብዙ ጊዜ ምንድነው የምንቸገረው ለምሳሌ አርባምንጭ ከተማ ምን ያህል ደጋፊ አለው ቢባል ፤ ድሬዳዋ ከተማ ምን ያህል ደጋፊ አለው ቢባል አዳማ ከተማ ምን ያህል አይታወቅም። አሁን ግን መረጃ ይኖረናል። በሚቀጥለው አመትም ይሄን መረጃ ላላወጡም በኤስ ኤም ኤስ ቴክስት እየላክን ደጋፊዎች መታወቂያቸውን እንዲያድሱ እንዲያወጡ እናደርጋለን ማለት ነው።”

ማህበሩ የተቋቋመው እግር ኳስን በእግር ኳስ ቋንቋ ብቻ እንደግፋለን ብለን ነው ፤ ደጋፊ ማህበራት የተቋቋሙትም ክለቦችን ለመደገፍ ነው ፤ ተባብረን ከሰራን የሀገራችንን እግር ኳስ መለወጥ እንችላለን ሲሉ አቶ ደነቀው ተናግረዋል።

የአጋርነት ስምምነቱ በየዓመቱ እየታደሰ የሚቀጥል ስለመሆኑን በመግለጫው ተጠቅሷል።

የሁሉም ክለብ ደጋፊዎች ለዚህ ተብሎ ለሁሉም ክለቦች የተዘጋጀውን መተግበሪያ ላይ ካሉበት ሆነው መጠቀም እንደሚችሉም ተገልጿል።

You Might Also Like

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ረጀብ ሚፍታህ ፣ነፃነት ገብረመድህን፣ ቢኒያም ገነቱ፣ ምኞት ደበበ እና አህመድ ሁሴን የጨዋታ እገዳ ሲጣልባቸው እንዲሁም በክለቦች ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ባህር ዳር ከተማ ቅጣት ተላልፎባቸዋል
Next Article ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ76 ቀናት ሀድያ ሆሳዕና ደግሞ ከ53 ቀናት በኋላ አሸንፈዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ኢስማዔል ዋቴንጋ በሁለት ዓመት ውል በይፋ አስፈረመ

hatricksport team By hatricksport team 7 years ago
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተሳታፊ ክለቦች ይፋ ተደርገዋል
​አማኑኤል ጎበና የወልዋሎ ኣራተኛ ፈራሚ ሆነ
የጨዋታ ዘገባ | ድሬዳዋ ከተማ በመጨረሻ ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ መቐለ 70 እ. ላይ ወርቃማ ድል ተቀዳጅቷል።
ሰበታ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ | ቀጥታ የውጤት መግለጫ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?