የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ረጀብ ሚፍታህ (ኢትዮጵያ ቡና) : ማከሰኞ ሚያዝያ 7 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ25ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 80 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ነፃነት ገብረመድህን (ስሁል ሽረ) : እሁድ ሚያዝያ 5 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ25ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+1 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 እንዲሁም አንቀፅ 66 ተቁ 1(ሀ) መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ቢኒያም ገነቱ (ወላይታ ድቻ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ወላይታ ድቻ – ኢትዮጵያ ቡና
- ሀዲያ ሆሳዕና – ወላይታ ድቻ
- መቐለ 70 እንደርታ – ወላይታ ድቻ
- ሃዋሳ ከተማ – ወላይታ ድቻ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -

4. ምኞት ደበበ(ፋሲል ከነማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ፋሲል ከነማ
- ፋሲል ከነማ – አርባምንጭ ከተማ
- ፋሲል ከነማ – ሃዋሳ ከተማ
- ኢትዮጵያ ቡና – ፋሲል ከነማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
5. አህመድ ሁሴን (አርባምንጭ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- አርባምንጭ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – አርባምንጭ ከተማ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ- አርባምንጭ ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ-መቻል
- መቻል – አርባምንጭ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
6. ሲዳማ ቡና ክለቡ ከባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ25 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሲዳማ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- መስፍን ታፈሰ
- ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን
- ዮሴፍ ዮሀንስ
- ብርሀኑ በቀለ
- ቶማስ ኢካራ
- መላኩ አስፋው
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
7. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ25 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ኮንኮኒ ሃፍዝ
- ረጀብ ሚፍታህ
- ዲቫይን ዋቹኩዋ
- ረጀብ ሚፍታህ
- ዳዊት ባህሩ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
8. ባህር ዳር ከተማ ክለቡ ከሲዳማ ቡናጋር በነበረው የ25ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ግጥሚያው 5 ደቂቃ ዘግይቶ ለመጀመሩ ምክኒያት እንደነበረ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
በመሆኑም በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 13.2 ተቁ 17 መሰረት ከለቡ ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


