1. አለሙ አዛናው (ፋሲል ከነማ-ወጌሻ) ማከሰኞ ህዳር 17 2017 ዓ.ም. ክለባቸው ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ8ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 89 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 13.3 ተ.ቁ 18 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገዱ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ፍቅሩ አለማየሁ (አዳማ ከተማ) እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ8ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 22 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ዋንጫ ቱት (ኢትዮጵያ መድን ) እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ8ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 22 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
4. ሚሊዮን ሰለሞን (ኢትዮጵያ መድን ) እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ8ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+2 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል # ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 እንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
5. ኢትዮጵያ መድን ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ8 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ መድን ቡድን ተጫዋች
- ዋንጫ ቱት በ22ኛው ደቂቃ
- ሚሊዮን ሰለሞን በ54ኛው ደቂቃ
- ያሬድ ካሳዬ በ76ኛው ደቂቃ
- መሃመድ አበራ በ85ኛው ደቂቃ
- ሚሊዮን ሰለሞን በ90+2ኛው ደቂቃ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
6. ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ (ኢትዮ ኤሌትሪክ) ክለቡ ከመቻል ጋር በነበረው የ8ኛ ሳምንት ግጥሚያ ጨዋታው ተጠናቆ ወደመልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያለ በኮሪደር ላይ የጨዋታ እና የውድድር አመራሮችን አጸያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ በፈጸመው ጥፋት በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት 3/ሶስት ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000 /ሶስት ሺህ / እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
7. አለሙ አዛናው (ፋሲል ከነማ-ወጌሻ) ክለቡ ከወላይታ ድቻ ጋር በነበረው የ8ኛ ሳምንት ግጥሚያ ባጠፉት ጥፋት ቀይ ካርድ በማየት እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ወደመልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያሉ የጨዋታ አመራሮችን አጸያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። ስለሆነም የቡድን አመራሩ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተላለፈባቸው ቅጣት በተጨማሪ ለፈጸሙት ሁለተኛው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት 3/ ሶስት ጨዋታ እንዲታገዱና ብር 3000 /ሶስት ሺህ / እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
ጥሪ
ለኢትዮ-ኤሌትሪክ የቡድን መሪ የፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሊያነጋግሮት ስለሚፈልግ ረቡዕ ህዳር 18 2017 10:30 ስዓት በድሬዳዋ ስታድዮም (ቅድመ ስብሰባ በሚደረግት ቦታ) እንዲገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ለአሰልጣኝ በረከት ገብረመድኅን (ስሁል ሽረ – ረዳት አሰልጣኝ) የፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሊያነጋግሮት ስለሚፈልግ ረቡዕ ህዳር 18 2017 በ 10፡00 ስዓት በድሬዳዋ ስታድዮም (ቅድመ ስብሰባ በሚደረግት ቦታ) እንዲገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል።


