By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “አንዳንድ ግለሰቦች አሉባልታ በመፍጠር እኔን የማይገልፀኝን ነገር ያስወራሉ” ፤ አሉባልታ በመፍጠር እኔን የማይገልፀኝን ነገር ያስወራሉ” አሰልጣኝ በሽር አብደላ ፦ የሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ሸገር ከተማየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግዜናዎችቃለመጠይቅ

“አንዳንድ ግለሰቦች አሉባልታ በመፍጠር እኔን የማይገልፀኝን ነገር ያስወራሉ” ፤ አሉባልታ በመፍጠር እኔን የማይገልፀኝን ነገር ያስወራሉ” አሰልጣኝ በሽር አብደላ ፦ የሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 1 year ago
Share
SHARE

“አንዳንድ ግለሰቦች አሉባልታ በመፍጠር እኔን የማይገልፀኝን ነገር ያስወራሉ”

“ህልሜ ትልቅ ነው ፤ ከሀገር ወጥቼ ማሰልጠን እፈልጋለሁ”

“ከዘንድሮው የዓምናው ውድድር የሚከብድ ይመስለኛል”

አሰልጣኝ በሽር አብደላ ፦ የሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ

- ማሰታውቂያ -

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተሞች ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

አዲስ አበባ ላይ በመደረግ ላይ ያለውን የምድብ ሀ ውድድር ሸገር ከተማ በስድስት ጨዋታዎች 16 ነጥቦችን አስመዝግቦ ምድቡን በመምራት ላይ ይገኛል።

ከተመሰረተ አጭር ጊዜ የሆነውን ይህን ክለብ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማስገባት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ስራዎችን ተሰርቶ አሁን ላይ ጥሩ የሊግ ጅማር በማድረግ ላይ ይገኛል።

ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት በመምራት ላይ የሚገኘው ወጣቱ አሰልጣኝ በሽር አብደላ አጠቃላይ የቡድኑን እንቅስቃሴ እና የአሰልጣኝነት ህይወቱን አስመልክቶ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ጋር ቆይታ አድርጓል።

እግርኳስን ገና በልጅነት ስለመጀመሩ የሚያነሳው በሽር እዚህ ደረጃ ለመድረስ ትልቅ ዋጋን ከፍያለሁ ይላል።

“ተወልጄ ባደኩበት የነገሌ አርሲ አካባቢ ነው 8ኛ ክፍል እያለሁ ኳስን መጫወትም ማሰልጠንም የጀመርኩት። በወቅቱ ከአካባቢዬ ትንሽ ራቅ በሚል አካባቢ ባለ በአንድ ፕሮጀክት ውስጥ ታቅፌ እሰራ ነበር። በሰፈሬ የሚጫወቱ ልጆች ስላልነበሩ ደግሞ እነሱን ይዤ አሰለጥን ነበር።”

በሽር ከፍ ባለ ደረጃ በክለቦች የመጫወትንም ዕድል አግኝቷል።በአዳማ ዩኒቨርስቲ በነበረበት 2002 ዓ.ም ወቅት ወልቂጤ ከተማ ከተማን የመጀመሪያው ክለብ አድርጎ ተቀላቀለ። በመቀጠልም ለቤንች ማጂ ፣ መቂ ከነማ ፣ ደደቢት በተስፋው እና በዋናው ቡድን ከተጫወተ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ፊቱን ወደ አሰልጣኝነት አዙሯል።

በልቶ ለማድር እንኳን ይቸገር በነበረ ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደግኩት የሚለው በሽር በጠንካራ ሰራተኝነት በሚወደው እግርኳስ ላይ መቀጠሉን ይገልፃል። የተጫዋችነት ዘመኑን ጫማውን ሰቅሎ ካጠናቀቀ በኋላ ታድያ ወደ አሰልጣኝነት የመጣበትን መንገድ እንዲህ ያወሳል። ነገር ግን በሽር ወደ አሰልጣኝን ከመምጣቴ በፊት በሌላ የህይወት መንገድ ውስጥ ገብቼ ነበር ይላል። ስደት።

“ከደደቢት ከተለያየሁ በኋላ ወደ መቂ ከተማ በውሰት ተመለስኩ። በኋላ ላይ ጓደኞቼ ለምን ስደት አንሞክርም አሉኝ።ከዛም ተስማምተን ወደ ግብፅ ሀገር አመራን። በ2008 ዓ.ም ማለት ነው። እዛም ግን በኳሱ ነበር የቀጠልኩት። በነበረኝ የአንድ አመት ቆይታ ሶስት አራት ክለቦችን ሞክሬ ነበር። ከዛን በሶስተኛ ዲቪዚዮን ለሚገኝ አንድ ክለብ አንድ አምስት ወር ያህል ከሰራሁ በኋላ ተመልሼ ወደ ሀገሬ መጣሁ።”

ወጣቱ አሰልጣኝ ያን ሁሉ ሳደርግ ቢኦፍቲ የሚባል የታዳጊዎች የፕሮጀክት ቡድን በስሬ ነበር ይላል። ግን የሚደግፉ ስፖንሰሮች ስለነበሩ ከሀገር ሲወጣ አልቆመም እርሱም እዚህ እያለ ከሚያገኘው ወርሐዊ ደመወዝ ላይ ፕሮጀክቱን በተለያዩ መንገዶች ሲደግፍ ነበር።

ቡድኑን ለመመስረት መነሻዬ የነበረው የአካባቢዬ ሁኔታ ነው የሚለው በሽር የሰፈሬ ልጆች በተለያዩ አጓጉል ነገሮች ላይ ስለነበሩ ያንን ለምን አላጠፋም በሚል ሀሳብ ስለመሆኑ ይናገራል።

ከዚህ ቡድን ወጥተው በከፍተኛ ሊግ ፣ ፕሪሚየር ሊግ ብሎም እስከ ብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ ተጫዋቾችም አሉ ብሏል።

ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ከግብፅ ወደ ሀገሩ የተመለሰ ሲሆን በ2009 ዓ.ም በነበረው የምዕራብ አርሲ ውድድር ላይ የነገሌ አርሲን ሁለተኛ ቡድን በመያዝ የአሰልጣኝነት ጉዞውን ሀ ብሎ ጀምሯል።

“የነገሌ አርሲን ሁለተኛ ቡድን ከያዝኩ በኋላ ምዕራብ አርሲን የወከለ እና ከ14 ከተሞች የተወጣጡ ተጫዋቾችን የያዘ ቡድን ይዤ በመላው ኦሮሚያ ውድድር ላይ ተሳተፍኩ። ከዛ በኋላ ነው የዋናው የነገሌ አርሲ ቡድን ምክትል ሆኜ የመስራት ዕድሉን ያገኘሁት። ለአምስት አመታት በቡድኑ ውስጥ ምክትል አሰልጣኝ ሆኜ ሰርቻለሁ።”

ከአምስት አመታት የምክትል አሰልጣኝነት ቆይታ በኋላ የነገሌ አርሲ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ የአሰልጣኝነት ቆይታውን አድርጓል።

በነገሌ አርሲ ቡድን በነበረው የሁለት አመታት ቆይታ ጠንካራ ቡድን በመገንባት ክለቡን የሊጉ ተፎካካሪ አድርጓል። በጠንካራ ተፎካካሪነት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ በሁለቱም አመታት ከጫፍ ቢደርስም በመጨረሻ ሳምንታት ላይ ሳይሳካ ቀርቷል።

የበሽርን የነገሌ አርሲ ቆይታ የተመለከቱ በርካታ ክለቦች የተጫዋቹ ፈላጊ ሆነው ብቅ ቢሉም በሽር ምርጫውን ሸገር ከተማን አድርጓል።

በጥቅማጥቅም ሳይቀር ከሌሎች ክለቦች የተሻለ ቀርቦልኝ ነው ሸገርን የመረጥኩት የሚለው በሽር ምክንያቴ የሚለውን እንዲህ አብራርቷል።

“ገና ዓመቱ ከመጀመሩም አስቀድሞ ነበር ጥያቄዎች የነበሩት ግን አንድ ሁለት አመት ራሴን እዚሁ ልይ በማለት እዛው ቀጠልኩ። 2015 ሶስተኛ ወጥቼ 2016 ደግሞ እዛው ነገሌ አርሲ መድገም ፈለግኩ።”

“2016ን ሁለተኛ ደረጃን ይዤ አጠናከኩ ግን አስቀድሞም ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ነበሩ። ነገር ግን ቆይ ከነገሌ አርሲ ጋር ደስተኛ ነኝ ብዬ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ቆየሁኜ። ውድድሩ ካለቀ በኋላ ሶስት እና አራት ክለቦች አናገሩኝ።”

“እኔም ክለቦቹ ምን አላቸው ? ስሌት ፤ ትክክለኛ የክለብ ቅርፅ እና ቀጣይ ዕቅድ እና ህልም ከግምት አስገብቼ የትኛው ነው የተሻለ በሚል ነው ራሴ የመረጥኩት ማለት ነው። ከሌሎቹ ክለቦች በተሻለ ደግሞ ሸገር ገፍቶ በመምጣት ድሬዳዋ ሄጄ ተጫዋቾችን ሁላ እንድመርጥ ነበር የነገሩኝ።”

“እናም ሸገርን የመረጥኩበት አንደኛ የክለቡ የአሰራር ቅርፅ እንዲሁም ቀጣይ ዕቅዱ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ነው። አንድ እና አንድ ይሄንን ቡድን ስረከብ ፕሪሚየር ሊግ አስገባ ነው የተባልኩት።”

ከሁሉም የከፍተኛ ሊግ ክለቦች አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅቱን የጀመረው ክለቡ በአሰልጣኝ በሽር አብደላ እየተመራ በባቱ ከተማ ላይ ለሁለት ወራት ያህል ጠንካራ ዝግጅት አድርጓል።

ቡድኑ በስብስቡ ከያዛቸው 30 ተጫዋቾች 28 አዳዲስ ፈራሚ ነበሩ የሚለው በሽር በሁሉም ረገድ ጥሩ የዝግጅት ጊዜ እንደነበረው ተናግሯል።

ሙሉ ለሙሉ የፈለጋቸውን ተጫዋቾች በተለያዩ ምክንያቶች ባያገኘም ጥሩ አቅም ያላቸውን ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ ቀላቅሎ የውድድር ዘመኑን ጀምሯል።

“ሁሉንም ያስፈረምኳቸውን ተጫዋቾች በራሴ መርጬ ነው። አብዛኞቹ አምና በኛ ምድብ ከነበሩ እና እንደውም ከከፍተኛ ሊጉ ከተሰናበቱ ክለቦች የመለመልኳቸው ናቸው። ቡድኑ አዲስ ከመሆኑ የተነሳ ነው እንጂ እንደውም እንደ ሀሳቤ እንደ አንድ ባለሙያ ከዚህም በላይ ለማድረግ ነበር የተዘጋጀነው ግን ቢሆንም አምና ስምንተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀውን ሸገር በዚህ ደረጃ ማስቀመጤ በራሴ እንድኮራ ነው የሚያደርገኝ”

ቡድኑን በጠበቀው ደረጃ ሊጉ ላይ አግኝቶት እንደሆነ ጥያቄ የቀረበለት በሽር ተጫዋቾቹ ጥሩ አቅም እንዳላቸው በመግለፅ ከጫና እና ለውጤት ከመጓጓት አንፃር በአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ላይ እንደነበረው ባይሆንም ቀስ በቀስ ግን ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻሎች አሉ ብሏል።

ለበርካታ ዓመታት ሊጉን የሚያውቀው በሽር የዘንድሮው ፉክክር ካለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር ምን ያህል ነው ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ከዘንድሮው የአምናው ከባድ ነበር ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል።

“ሊጉን በደንብ አውቀዋለሁ የትኛው ዲፓርትመንት ምን አይነት ተጫዋች እንደሚፈልግ ሊጉ ምን አይነት ጫና እንዳለው በሚገባ አውቀዋለሁ። እውነት ለመናገር ቁጭ ብዬ ሌሎች ቡድኖች የሚያደርጉትንም ጨዋታ ስለማይ ዘንድሮ እውነት ለመናገር የአምና ውድድር የሚከብድ ይመስለኛል ከዘንድሮው”

በመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ግቦችን ለማስቆጠር ተችግረን ነበር የሚለው በሽር አንደኛው ምክንያት ሸገር ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል ፤ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት ቆርጦ ነው የተነሳው በሚል በይበልጥ በመከላከል ላይ በተመሰረተ አጨዋወት ነበር የሚገጥሙን ሲል ተናግሯል።

በሀገራችን ክለቦች ላይ በስፋት ከሚስተዋሉ እንከኖች መካከል የክለብ አመራሮች ለክለቦቻቸው የሚሰጡት ትኩረት ነው። ጥሩ የክለብ አመራር ያለው እና በሚገባ መንገድ ቡድኑን የሚደግፍ አመራር ያለው ክለብ ለውጤታማነቱ ትልቁን እርምጃ ተራምዷል ማለት ይቻላል።

አሰልጣኝ በሽርም ስለ ሸገር ከተማ የክለብ አመራሮች ድጋፍ ተከታዩን ተናግሯል። “በዚህ ረገድ ክለቡ እንከን የለውም ማለት ይቻላል።ሙሉ በሙሉ ብለህ ባትደመድምም ከሌሎች ክለቦች ይሻላል ፤ በጣም ክትትል አለው ብቻ ጥሩ ነው አሪፍ ነው።አመራሮቹ ስፖርቱን ይፈልጉታል። በተለይም በዚህ አጋጣሚ ደግሞ የክለቡ ፕሬዚዳንት አቶ ናስር ሁሴንን ማመስገን እፈልጋለሁ። በጣም ነው የሚከታተለው ጉጉት አለው።ክለቡ ፕሪሚየር ሊግ እንዲገባ ይፈልጋል።በአጠቃላይ ያለው ድጋፍ ጥሩ ነው።”

የቡድኑ ተጫዋቾች ክለቡን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማስገባት ከፍተኛ ጉጉት አላቸው የሚለው አሰልጣኝ በሽር እኔ ውስጥ ያለው ከፍተኛ ፍላጎት እነርሱ ጋርም አለ ሲል ገልጿል። “ልጅ አባትን ይመስላል” በማለትም የተጫዋቾቹን ስሜት ለመግለጽ ሞክሯል።

ከፍተኛ ተነሳሽነት ፣ ትክክለኛ የስፖርተኛ ባህሪ ፤ ታዛዦች እና ነገን በትልቅ ተስፋ የሚያልሙ ሲልም የሚያሰለጥናቸውን ተጫዋቾች ገልጿቸዋል።

አሰልጣኝ በሽር አብደላ ምንም እንኳን ያለውን አቅም አስቀድሞ በነገሌ አርሲ አሁንም በሸገር ከተማ እያሳየ ቢሆንም ካደኩበት ሰፈር ጀምሮ ነው ያሉት በሚላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ስም የማጥፋት ስራን ሊሰሩበት እንደሚሞክሩ ገልጿል።

ይህ ነገር ሊያጋጥመኝ እንደሚችል አንድ ባለሙያ አስቀድሞ ነገሮኝ ነበር ይላል አሰልጣኝ በሽር። “አንድ ትልቅ ሰው ሙያው ያለ አምና ያለኝን ልንገርህ አሁን ይረባረቡበሀል በብዙ ነገር ይመጡብሀል አንደኛ ከዳኛ ጋር አትነካካ ማለት አትጨቃጨቅ ሁለተኛ ደግሞ ከቻልክ ደግሞ ከነዛ ሰዎች ራቅ በሩቅ ሰላም በላቸው ብሎኝ ነበር።”

ከሰው ጋር መግባባት የምወድ እና የዋህ ነኝ ይህንን ቀርበው ያዩኝ ይመሰክራሉ የሚለው አሰልጣኝ በሽር ሙያው ውስጥ ያሉም ከሙያው ውጪ ያሉም ናቸው አሁን ላይ ይህንን የሚያደርጉት ብሏል።

በወጣትነት ዕድሜዬ አሰልጣኝ ሆኜ በዛም ላይ ውጤታማ መሆኔን ሲመለከቱ ያ ነገር ያልተዋጠላቸው ሰዎች ናቸው እኔን የማይገልፀኝን አሉባልታ በመፍጠር የሚያስወሩት ብሏል።እኔ ቦታ አልሰጠውም ግን በሽር ማነው ለሚሉ የተሳሳተ አመለካከት እንዲይዙ ስለማልፈልግ ነው ሲልም ያክላል።

እግርኳስ ከምንም ነገር የፀዳ ነው የሚለው አሰልጣኝ በሽር ይሄን ጠንቅቄ የማውቅ ሰው ነኝ ሙያው ምን እንደሚፈልግ የማውቅ ነኝ ከታች ጀምሬ በብዙ ልፋት እና መከራ እዚህ የደረስኩት ሲል ተናግሯል። በፕሪሚየር ሊጉ እስከ ብሔራዊ ቡድን የደረሱ ተጫዋቾች በርሱ ስር ማለፋቸውንም መዘንጋት የለበትም ሲል ያክላል።

በተለያዩ መንገዶች በማንነቴ ጭምር እየመጡ ምንም ማረጋገጫ የሌላቸውን አሉባልታዎች በመፍጠር ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ያነሳሉ የሚለው አሰልጣኝ በሽር ሰውን ቀርበው ሳያዩ መፈረጅ ተገቢ አይደለም ፤ በፊት ከሩቅ አይተውኝ የማይሆን ነገር ሲናገሩ የነበሩም ቀርበው ሲያዩኝ እና የኔን ትክክለኛ ማንነት ሲረዱ ስህተት እንደነበሩ አውቀዋል ሲል ተናግሯል።

አሁንም ቢሆን ዝም ብሎ ከመፍረድ ቀርበው ቢያዩ መልካም ነው በተጨማሪም እግርኳስ ከማንኛውም የኃይማኖት እና የብሔር ጉዳዮች ነፃ መሆኑን ሊረዱ ይገባል ሲል አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል።

ግን ይላል አሰልጣኝ በሽር ግን ማንም ምንም ቢል ወደ ኋላ የምልበት ምክንያት የለም። “ማንም ምንም ቢል ምንም አይመስለኝም። ከመንገዴ ማንም አያስቀረኝም። እንደዚህ አይነት ነገሮች ባይነሱ ደስ ይለኛል። ምክንያቱም ይህ አይነት መገፋፋት ለማንም አይጠቅምም።”

በኛ ሀገር እግርኳስ ደጋፊ ከ12 አልፎ 13ኛ ተጫዋች ሆኗል የሚለው አሰልጣኝ በሽር ባለፉት ጨዋታዎች ላይ በርካታ ደጋፊዎች ካላቸው ክለቦች ጋር መጫወቱን በመጥቀስ የሸገር ከተማ ደጋፊዎችም በቀጣይ በተሻለ ቡድናቸውን እየደገፉ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ የሚደረገውን ጉዞ እንዲደግፉ ጥሪም አቅርቧል።

ወጣቱ አሰልጣኝ በቀጣይ ትልቅ ግብ እንዳለው እና ያንን ከማሳካትም ምንም የሚያግደው ነገር እንደማይኖር ጠቁሟል።አሁን ግን ይላል አሰልጣኝ በሽር አሁን ላይ አንድ እና አንድ ዓላማ ነው ያለኝ ይላል።

“እኔ ትልቅ ህልም ነው ያለኝ። አሁን ላይ አንድ እና አንድ ሸገርን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማስገባት ነው። ቅድም እንደነገርኩህ በርካታ ጥያቄዎች ነበሩ የእጅ እንስጥህ የሚሉ ሁላ ነበሩ። ግን ደግሞ የኔን ጥቅም እና የኔን ደመወዝ ብቻ አስተካክዬ ተጫዋቾች ደግሞ እዚህ ጋር ደመወዝ የማይከፈላቸው ከሆነ ከባድ ነው ለህሊናዬም። የኔን ብቻ አይደለም ተጫዋቾቼም በልተው ጠጥተው ማደር አለባቸው።”

“ከነሱም አልፎ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ናቸው ልጆች አሏቸው። በጊዜ ደመወዝ መክፈል የሚችል እና በጊዜ ለስፖርተኛው ደራሽ መሆን የሚችል ክለብ ነው የሚል ዕምነት ስላለኝ ነው ሸገርን የተቀላቀልኩት።እናም አሁን ላይ አንድ እና አንድ ሸገርን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ስለማስገባት ነው የማስበው ከዛ በኋላ እንግዲህ ፈጣሪ ያውቃል።”

“ህልሜ ትልቅ ነው። ከሀገር ወጥቼ ማሰልጠን እፈልጋለሁ። እንዳልኩህ አሰልጣኝነትን በልጅነቴ ስለገባሁበት ራሴን ለማሻሻል ቀን ከሌት እሰራለሁ። ከብዙ ሰዎች ጋርም እግባባለሁ በሚያጋጥሙኝ ነገሮች ዙሪያ በሙያው ትላልቅ ስራን ከሰሩ አሰልጣኞች ምክሮችን እጠይቃለሁ እቀበላለሁ።በሀገር ውስጥ ተገድቤ መቅረት አልፈልግም ህልሜም እንደዚህ አይደለም። እንዲህ ስል ለጉራ አይደለም። ልክ እንደ እነ ፍሬው ኃይለገብርኤል ከሀገር ወጥቼ ማሰልጠን ነው የምፈልገው። እስከ ውጪ ሄደን ለማሰልጠን ምንም የሚከለክለን ነገር የለም አቅም አለን።”

በዕቅዴ መሰረትም እየተጓዝኩ ነው የሚለው አሰልጣኝ በሽር ከፈጣሪ ጋር በእርግጠኝነት አሳክቼ ኢንተርናሽናል አሰልጣኝ እሆናለሁ ብሏል።

የኛ እና የሌሎች አፍሪካ ሀገራት እግርኳስ ልዩነቱ ትንሽ ነው የሚለው በሽር በግብፅ በነበረኝ ቆይታ የተረዳሁት ነገር ልዩነቱ ወጥ የሆነ ፕሮፌሽናል አሰራር አላቸው በሂደት ነው የሚሰሩት ያ ነው እንጂ በሌሎች በሌሎች ብዙም ልዩነት የለውም ይላል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ሲደረጉ የምድብ ሀ መሪው ሸገር ከተማ በመጪው ረቡዕ 9:00 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ጨዋታውን ያደርጋል።

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የስምንተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Next Article ለአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራርነት ሰራዊት ፍቅሬ ታስቦ ማስተዋል ወንድወሰን ተመረጠች

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሊግ ካምፓኒዲ ኤስ ቲቪየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎች

LIVE | የ ዲኤስቲቪ እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ስምምነት !

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 5 years ago
የጨዋታ ዘገባ| ጅማ አባ ጅፋር ከወራጅ ቀጠና ስጋት የራቀበትን ድል ድሬደዋ ላይ አሳክቷል
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ኢያሱ መርሃ ጽድቅ ከቦታቸው እንዲነሱ ተወሰነ
አዳማ ከተማ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉን ለመቅጠር ወሰነ
ዝውውር | ከሳምንታት በፊት ከመቐለ ከተማ ጋር የተለያየው ዮሴፍ ደንገቶ ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሏል።
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?