በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት አራተኛ መርሀግብር ሀድያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ ተገናኝተው ጨዋታው በወላይታ ድቻ የ1 – 0 አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወቃል።
ከጨዋታው በኋላም የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች በተቀመጡባቸው የስታድየሙ ክፍሎች አካባቢ ያሉ ወንበሮች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል። የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በነበሩት አካባቢ 105 ወንበሮች እንዲሁም የሀድያ ሆሳዕና ደጋፊዎች በነበሩበት ደግሞ 65 ወንበሮችን ስለመነቃቀላቸው ሪፖርት ቀርቧል።
ይህንን ጉዳይ የተመለከተው የሊጉ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በሁለቱም ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን የተነቃቀሉትን ወንበሮች እንዲያሰሩ ወይም የስታድየሙ ባለቤት አሰርቶ የሚያቀርበውን ዋጋ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።


