የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ይፋ ሲሆኑ ሁለት ተጫዋቾች የጨዋታዎች ዕገዳ ተላልፎባቸዋል።
የወልዋሎ አዲግራቱ አምበል እና ግብ ጠባቂ በረከት አማረ ክለቡ ከኢትዮጵያ መድኅን ጋር ከነበረው ጨዋታ በኋላ የጨዋታውን ዳኛ አፀያፊ ስድብ በመሳደቡ የቀይ ካርድ ተመልክቷል።
በተጨማሪም የሀዋሳ ከተማው እንየው ካሳሁን ክለቡ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ከነበረው ጨዋታ በኋላ የተጋጣሚ ቡድን አባላትን በምልክት አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት ቀርቦበታል።
በዚህም ሁለቱም ተጫዋቾች እያንዳንዳቸው የሶስት ጨዋታ እና የሶስት ጨዋታዎች እገዳ ተላልፎባቸዋል።
- ማሰታውቂያ -
በረከት አማረ ክለቡ ወልዋሎ አዲግራት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ከአርባምንጭ ከተማ እና ከፋሲል ከነማ ጋር የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች እንዲሁም እንየው ካሳሁን ክለቡ ሀዋሳ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ፣ ከወላይታ ድቻ እና መቀሌ 70 እንደርታ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚያልፏቸው ይሆናል።
በተያያዘም ባህርዳር ከተማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታዎቻቸው ላይ አምስት አምስት ተጫዋቾቻው የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርድ በመመልከታቸው እያንዳንዳቸው የ5 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።


