በክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ መሰረት ክለቦች የየወሩን ጥቅል የደመወዝ ሪፖርት ወር በገባ እስከ 10 ቀን ማሳወቅ እንዳለባቸው ተጠቅሷል። መመሪያው ከሚያዘው ውጪ የፕሪሚየር ሊጉ አራት ክለቦች ሪፖርት ማድረግ ከነበረባቸው ከ12 እስከ 27 ቀናት በላይ በመቆየት ሪፖርት አድርገዋል።
የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 01/2016 አንቀፅ 9 መሰረት በአራት ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በዚህ መሰረትም :-
ሀዋሳ ከተማ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ12 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 70,000(ሰባ ሺህ ብር)
- ማሰታውቂያ -
አዳማ ከተማ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ23 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 180,000(አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር)
አርባምንጭ ከተማ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ24 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 190,000(አንድ መቶ ዘጠና ሺህ ብር) እንዲሁም
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ27 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 220,000(ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ብር) ተቀጥተዋል።