‘በሀገረ ጀርመን ያገኘሁትን ልምድ እና እዉቀት ወደ ትዉልድ ሀገሬ አምጥቼ ወጣት ተጫዋቾችን ለአዉሮፓ እግርኳስ ለማብቃት ትልቅ ህልም ነበረኝ” የ3 Point National Academy project ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ ሳሙኤል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ15፣ 17 እና 20 ዓመት በታች የዕድሜ እርከኖች ወጣቶችን በማሰልጠን እና ለብሔራዊ ቡድኖቻችን፤ አልፎም ለታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ገበያ ለማብቃት በማሰብ የሚገነባው የወጣቶች ብሔራዊ አካዳሚ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበት እና በአካዳሚው አስተዳደር ላይ በጋራ ለመስራት ከጀርመን ድርጅት ጋር የስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት ፕሮግራም በዛሬዉ ዕለት ሰኞ ህዳር 13/2014 ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሂዷል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም የ3 Point National Academy project መስራች እና ባለቤት ትዉልደ ኢትዮጵያዊዩ አቶ ቴዎድሮስ ሳሙኤል ስምምነቱን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃዎችን በስፍራዉ ለታደሙት የሚዲያ አካላት ገለፃ አድርገዋል።
ዝርዝሩን ከቆይታ በኋላ ይዘን የምንመለስ ይሆናል
አስተያየት ይስጡ