መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | የአብዱልከሪም ወርቁ ብቸኛ ግብ ወልቂጤ ከተማ የአመቱን የመጀመሪያ ድል እንዲያገኝ አስችሎታል
ሀዋሳ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወልቂጤ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የአብዱልከሪም ወርቁ ብቸኛ ግብ ወልቂጤ ከተማ የአመቱን የመጀመሪያ ድል እንዲያገኝ አስችሎታል

አጋራ
አጋራ

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማን ከ ሀዋሳ ከተማ ከ12 ሰአት ጀምሮ አገናኝቶ ጨዋታው በወልቂጤ ከተማ የ1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል ።

በሁለቱም በኩል ከሶስተኛ ሳምንት ጨዋታቸው ለውጦች አድርገው የገቡ ሲሆን በወልቂጤ ከተማ በኩል ሶስት ቅያሪዎችን በማድረግ የገቡ ሲሆን እስራኤል እሸቱ ፤ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና ያሬድ ታደሰ ወደ ቋሚ አሰላለፉ መካተት የቻለለ ተጫዋቾች ሲሆን በሀዋሳ ከተማ በኩል በሶስተኛ ሳምንት ሲዳማ ቡናን ካሸነፈው ቡድን አንድ ቅያሪ ብቻ በማድረግ ሄኖክ ድልቢን ወደ ቋሚ አሰላለፍ አካተው ጨዋታውን ጀምረዋል ።

የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ እምብዛም ሳቢ ያልነበረ ሲሆን በሁለቱም በኩል ወደ ግብ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶች ያን ያህል አልነበሩም ። የጨዋታውን የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ለመመልከት 39 ደቂቃዎችን መጠበቅ የግድም ሆኖ ነበር ። በዚህ ደቂቃ ላይ በሀዋሳ ከተማ በኩል በፈጣን መልሶ ማጥቃት በቀኝ መስመር የገባው መስፍን ታፈሰ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ በአይቮሪኮስታዊው የግብ ዘብ ሲልቭያን ግቦሆ ተመልሶበታል ። ሌላ ተጨማሪ የግብ ሙከራም ሳንመለከት የመጀመሪያ የጨዋታ አጋማሽ ተጠናቀቀ ።

የሁለተኛው አጋማሽ ከጅማሮው ከመጀመሪያው የተሻለ እንቅስቃሴን ያስመለከተ ነበር ። በተለይም ክትፎዎቹ ወደ ፊት በመሄድ ረገድ ከተጋጣሚያቸው በተሻለ መልኩ መንቀሳቀስ ችለዋል ።

የሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ 19 ደቂቃዎች በኋላ የጨዋታው የመጀመሪያ ግብ ተቆጠረ ። በጨዋታው ጥሩ እየተንቀሳቀሰ የነበረው አብዱልከሪም ወርቁ በሀዋሳ ከተማ ተጨዋቾች ስህተት የተገኘውን ኳስ ተጠቅሞ 64ኛ ደቂቃ ላይ ክትፎዎቹን መሪ አደረገ ።

ከግቧ መቆጠር በኋላ የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ጥረቶችን ያደረጉት ሀዋሳ ከተማዎች በተለይም በብሩክ በየነ አማካኝነት ጥሩ የግብ ዕድልን ማግኘት ቢችሉም ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል ።

77ኛ ደቂቃ ላይ የሀዋሳ ከተማው ተጫዋች አብዱልባሲጥ ከማል በግብ አስቆጣሪው አብዱልከሪም ወርቁ ላይ በሰራው ጥፋት በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ። ከ10 ደቂቃዎች በኋላም የወልቂጤ ከተማው ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ መድሀኔ ብርሀኔ ላይ በሰራው ጥፋት ልክ እንደ አብዱልባሲጥ ሁሉ በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ሊወጣ ችሏል ።

በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ሀዋሳ ከተማዎች በመስፍን ታፈሰ እና ቸርነት አውሽ አማካኝነት ግቦችን የማስቆጠር ዕድሎችን መፍጠር ቢችሉም ኳስን ከመረብ ማገናኘት ሳይችሉ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ችሏል ።

በዚህም መሰረት ወልቂጤ ከተማዎች ነጥባቸውን ወደ 5 ማሳደግ ሲችሉ ሀዋሳ ከተማዎች ባሉበት 6 ነጥብ የሚቆዩ ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...