*…ምክትሏም እንድትቀጥል
ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው …
ላለፉት በርካታ ወራት በብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ስር የተካተቱት አምስት አባላት መበተናቸው ተሰማ።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ የኮሚቴው ሰብሳቢ ሸዋንግዛው ተባባል ሲቀር ምክትሏ ሊዲያ ታፈሰ እና የኮሚቴ አባላቱ ክንዴ ሙሴ፣ ክንፈ ይልማና ለማ ንጉሴ ዛሬ ከኮሚቴው መሰናበታቸው ታውቋል።
ፌዴሬሽኑ ከሰብሳቢው ሸዋንግዛው ተባባል ጋር ለመቀጠል ሲወስን ምክትል የነበረችውን ሊዲያን ማሰናበቱ ያልተዋጠላቸው አካላት የፕሬዝዳንቱ ኢሳያስ ጅራና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔን ለማስቀየር ሽምግልና መጀመራቸው አብዛኞቹ ዳኞችን አስደንግጧል።
- ማሰታውቂያ -
2018 ችግር ቢፈጠር ሽማግሌዎቹ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ አመራሮቹም ውሳኔያቸው በጥናት የተወሰነ በመሆኑ አቋማቸውን ይቀይራሉ ተብሎ አይጠበቅም የሚሉ ዳኞች በርክተዋል።
20 ክለቦች የሚሳተፉበትን የ2018 የኢትዮጶያ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ የሁሉንም ሊጎች ውድድር በሰላም ለማጠናቀቅ ኮሚቴውን በመበተን ጠንካራ ባለሙያዎችን እንደገና ለማካተት የተደረገው የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ድጋፍ የሚቸረው ሆኗል።
በነበረው የዳኝነት ውዝግብ፣ በዳኞች ሲፈሩ የቆዩት የኮሚቴ አባላቱ እያሉ አመቱ በሰላም መጠናቀቁ የሚገርማቸው የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የአመቱ ኮከብ ዳኛ ምርጫ ላይ እገሌ ካልሆነ ጥርስ እንሳበራለን አንገቴን እታነቃለው በሚል ጎራ የለዩ አባላት 2018 ዳግም እንዲቀጥሉ መፈቀድ እንደሌለበት ይናገራሉ።
ኮሚቴውን ሲመራ የነበረው ሸዋንግዛው ተባባል በቦታው መቀጠሉን በአዎንታዊ ጎን የወሰዱት ወገኖች በኮሚቴው ውስጥ ጠንካራ አባላት ከተካተቱ ያለውን አቅም ሊያወጣ ይችላል በሚል ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።


