የትግራይ ስፖርት ኮሚሽንን ለመደገፍ እና መልሶ ለማደራጀት የሚያስችል እንቅስቃሴ ተጀመረ ።
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የጁንታው የህወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ እና በሀገር ላይ በፈፀመው ክህደት በትግራይ ክልል ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ይታወቃል ።
የክህደት ቡድኑ በተለይም እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል እንደሚባለው ትምህርት ቤቶችን እና የጤና ተቋማትን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገር ሀብትና ጉልበት የፈሰሰባቸውን መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ አድርጓል ፣ የመንግስት ተቋማትን አፈራርሷል ፣ በሰብዓዊ ላይ ከፍተኛ ቀውስ አስከትሏል ።
በነበረው የሰላም ችግር ምክንያት ከተጎዱ የመንግስት ተቋማት መካከል የትግራይ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አንዱ ሲሆን ኮሚሽኑ ለበርካታ ዓመታት ያፈራቸው ሀብቶች ፣ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች እና የስፖርት ትጥቆች ወድመዋል ።
በመሆኑም የክልሉን ስፖርት ኮሚሽን መልሶ ለማደራጀት እና ለማቋቋም የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ።
ግብረ ሃይሉ በኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ የሚመራ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክን ጨምሮ የሀገረ አቀፍ ስፖርት ማህበራትን ፣ ተጠሪ ተቋማትን እና የክልልና ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽንን ያካተተ ነው ።
በቀጣይም የተቋቋመው ግብረሃይል የደረሰበትን ደረጃ እና የሚያደርገውን ድጋፍ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ።
መረጃው የኢፌዴሪ ስፖርትም ኮሚሽን ነው።
አስተያየት ይስጡ