- ደስታ ዋሚሾ(ሀዲያ ሆሳዕና) የመታወቂያ ቁጥር EFF-17-0021 ረቡዕ ጥቅምት 27 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የ7ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+9 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

- ሀዲያ ሆሳዕና ክለቡ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የ7 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 ሰመረ ሀፍተይ
2 ደስታ ዋሚሾ
3 እዮብ ዓለማየሁ
4 ቃለአብ ውብሸት
5 ካሊድ መሀመድ
6 ዳግም ንጉሴ
7 ኢያሱ ደስታ
8 በረከት ወልደዮሐንስ
9 ደስታ ዋሚሾበተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
የሰባተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች


