የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ፀጋዬ ኪዳነ ማሪያም(ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) ረቡዕ ጥር 7 2017 ዓ.ም. ክለባቸው ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ14ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+2 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 13.3 ተ.ቁ 18 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ዮናስ ለገስ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ማከሰኞ ጥር 6 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ባደረገው የ14ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 89 ኛ ደቂቃ ላይ ከስፖርታዊ አድራጎት ውጭ በመሆን/በመጫወት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -

3. አማኑኤል ኤርቦ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
ቅዱስ ጊዮርጊስ – አርባምንጭ ከተማ
መቻል – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቅዱስ ጊዮርጊስ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
ቅዱስ ጊዮርጊስ – ስሁል ሽረ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
4. ሄኖክ ተወልደ (ስሁል ሽረ) ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነበረው የ14ኛ ሳምንት ግጥሚያ ጨዋታው ተጠናቆ ወደመልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያለ የተጋጣሚ ቡድንደጋፊዎችንና ከተጠባባቂ ውጪ (over bench)ተጨዋቾችን በምልክትና በድምፅ አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ በፈጸመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት 3/ሶስት ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3 000 / ሶስት ሺህ / እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
5. አሮን አንተር (ቅዱስ ጊዮርጊስ) (ለ2017 የውድድር ዘመን ያልተመዘገበ)/ ክለቡ ከስሁል ሽረ ጋር በነበረው የ14ኛ ሳምንት ግጥሚያ ጨዋታው ተጠናቆ ክለቦቹ ወደመልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያሉ ከተጠባባቂ ውጪ (over bench)ተጨዋቾች ከሚቀመጡበት ቦታ ላይ ሆኖ የተጋጣሚ ቡድንን ተጫዋች ለመደባደብ እንደተጋበዘና በፀጥታ ኃይሎች ተይዞ የተገላገለ ስለመሆኑን ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ በፈጸመው ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 10 አንቀፅ 35 በተቁ 2 መሠረት ከ15ኛ ሳምንት ጀምሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጋቸውን 5/አምስት/ ተከታታይ ጨዋታዎች ስታድየም ገብቶ እንዳይመለከት የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


