የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. አቤኔዘር ዮሐንስ (ፋሲል ከነማ) : ክለቡ ከ ሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ15ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 71 ኛ ደቂቃ ላይየተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 እንዲሁም አንቀፅ 66 ተቁ 1(ሀ) መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3ዐዐዐ /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ሄኖክ ሐሰን (ድሬደዋ ከተማ) : ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ15ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 22 ኛ ደቂቃ ላይየተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 እንዲሁም አንቀፅ 66 ተቁ 1(ሀ) መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ይገዙ ቦጋለ (አርባምንጭ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ካርድ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ማሰታውቂያ -
- አርባምንጭ ከተማ-ባህርዳር ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ-ሸገር ከተማ
- ሀዲያ ሆሳዕና-አርባምንጭ ከተማ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-አርባምንጭ ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ-መቻል
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
4. በረከት ጥጋቡ (ባህርዳር ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- አርባምንጭ ከተማ-ባህርዳር ከተማ
- ባህርዳር ከተማ-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ባህርዳር ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ምድረ ገነት ሽረ -ባህርዳር ከተማ
- ባህርዳር ከተማ-መቐለ 70 እንደርታ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
5. ሄኖክ ገብረህይወት (ኢትዮ ኤሌትሪክ ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ኢትዮ ኤሌትሪክ -አርባምንጭ ከተማ
- ኢትዮጵያ ቡና-ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ -ነገሌ አርሲ
- ባህርዳር ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
6. ዳግም ንጉሴ (ሀዲያ ሆሳዕና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ሀዲያ ሆሳዕና-ኢትዮጵያ መድን
- ሸገር ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዲያ ሆሳዕና
- ሃዋሳ ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ምድረ ገነት ሽረ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
7. ኢዮብ አለማየሁ (ሀዲያ ሆሳዕና): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ባህርዳር ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ቅዱስ ጊዮርጊስ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ወላይታ ድቻ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ምድረ ገነት ሽረ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
8. ድሬደዋ ከተማ ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ15 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የድሬደዋ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ሄኖክ ሐሰን
- ዘርዓይ ገብረስላሴ
- ሲያም ሱልጣን
- አብዩ ካሳዬ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000/ አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
9. ፋሲል ከነማ ክለቡ ከሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ15 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የፋሲል ከነማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- አቤኔዘር ዮሐንስ
- ምኞት ደበበ
- አቤኔዘር ዮሐንስ
- ቢኒያም ጌታቸው
- ዳግም አወቀ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ /እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
10. ሀዲያ ሆሳዕና ክለቡ ከምድረ ገነት ሽረ ጋር ባደረገው የ15 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ተመስገን ብርሃኑ
- ኢዮብ አለማየሁ
- ዳግም ንጉሴ
- ተፈራ አንለይ
- ዳግም ወንድሙ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
11. አዲሱ ተስፋዩ (ምድረ ገነት ሽረ) : ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ15ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+5 ኛ ደቂቃ ላይ ተጋጣሚን ሆን ብሎ በቦክስ ስለመማታቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
12. ወንድሜነህ ደረጀ (ባህርዳር ከተማ) : ክለቡ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ባደረገው የ15ኛ ሳምንት ጨዋታ ጨዋታው ተጠናቆ ወደመልበሻ ክፍል በሚገቡበት ወቅት የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች ለመማታት ሲጋበዝ እንደነበር ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 61 በተቁ 2 (ለ)መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ ብር 5000 /አምስት ሺህ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
የመርሀ ግብር ለውጥ
ማከሰኞ ጥር 12/2018 ፋሲል ከነማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ከበዓል ጋር በተያያዘ ምክኒያት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ እና ወደፊት በሚወጣ መርሃ ግብር በተስተካካይ ጨዋታ እንዲደረግ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


