መነሻ ገጽ ዜናዎች የ18ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የ18ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

አጋራ
አጋራ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. አሳምነው ገብረወልድ (ኢትዮ ኤሌትሪክ ) /ረዳት አሰልጣኝ : ክለባቸው ከ ሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ18ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 89 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ።
ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 6 ጨዋታ እንዲታገዱ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ዮናስ ለገስ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : ክለቡ ከ ነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ18ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 48ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

3. ኤፍሬም ታምራት (አርባምንጭ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  • አርባምንጭ ከተማ-ሸገር ከተማ
  • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባምንጭ ከተማ
  • አርባምንጭ ከተማ ፋሲል ከነማ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-አርባምንጭ ከተማ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

4. ቢኒያም ካሣሁን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ።

  • መቐለ 70 እንደርታ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
  • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ሀዲያ ሆሳዕና
  • ኢትዮ ኤሌትሪክ -ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገሌ አርሲ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

5. ወንድማገኝ ማዕረግ (ሃዋሳ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ።

  • ሲዳማ ቡና-ሃዋሳ ከተማ
  • ሃዋሳ ከተማ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ሃዋሳ ከተማ
  • ሃዋሳ ከተማ-መቻል
  • ሃዋሳ ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

6. በረከት ሳሙኤል (ሃዋሳ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  • ሲዳማ ቡና-ሃዋሳ ከተማ
  • ሸገር ከተማ-ሃዋሳ ከተማ
  • ሃዋሳ ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
  • አርባምንጭ ከተማ-ሃዋሳ ከተማ
  • ሃዋሳ ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅካት ብር 1500 እንዲከፍል ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

7. አሚኑ ነስሩ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) : ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  • ባህርዳር ከተማ-ቅዱስ ጊዮርጊስ
  • ቅዱስ ጊዮርጊስ-ኢትዮጵያ መድን
  • ቅዱስ ጊዮርጊስ-ሀዲያ ሆሳዕና
  • ቅዱስ ጊዮርጊስ-ምድረ ገነት ሽረ
  • ፋሲል ከነማ-ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

8. ከቤ ቡዙነህ (ነገሌ አርሲ): ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል

  • ነገሌ አርሲ-ሸገር ከተማ
  • ምድረ ገነት ሽረ -ነገ አርሲ
  • ሃዋሳ ከተማ-ነገሌ አርሲ
  • ነገሌ አርሲ-ሲዳማ ቡና
  • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ነገሌ አርሲ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

9. ሃዋሳ ከተማ ክለቡ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ባደረገው የ18 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሃዋሳ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት

  1. በረከት ሳሙኤል
  2. ወንድማገኝ ማዕረግ
  3. ጌታነህ ከበደ
  4. ዝያድ ከድር
  5. እስራኤል እሸቱ

በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

የተሰተካካይ ጨዋታ መርሀ ግብር

ከበዓል ጋር በተያያዘ ምክኒያት ለሌላ ጊዜ ተላልፎ የነበረው የፋሲል ከነማ ና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ ሰኞ የካቲት 2 2018 ከሰዓት በ9:0ዐ በአዲስ አበባ ስታድየም እንዲደረግ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...