የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ስንታየሁ ወለጬ (ምድረ ገነት ሽረ) : ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ17ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 78 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ይሁን እንዳሻው (አርባምንጭ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- አርባምንጭ ከተማ-አዳማ ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ-ሸገር ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ-ኢትዮጵያ ቡና
- አርባምንጭ ከተማ-መቐለ 70 እንደርታ
- አርባምንጭ ከተማ-ፋሲል ከነማ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
3. ካሌብ አማንክዋህ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ወላይታ ድቻ
- ሲዳማ ቡና-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ቡና-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
4. ሀብታሙ ጉልላት (ቅዱስ ጊዮርጊስ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ነገሌ አርሲ-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ባህርዳር ከተማ-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሲዳማ ቡና-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ-ምድረ ገነት ሽረ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
5. ቦና ቦካ (ነገሌ አርሲ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ኢትዮ ኤሌትሪክ -ነገሌ አርሲ
- ነገሌ አርሲ-ሽገር ከተማ
- ምድረ ገነት ሽረ -ነገሌ አርሲ
- ነገሌ አርሲ-ወላይታ ድቻ
- ነገሌ አርሲ-ሲዳማ ቡና
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
6. ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን (ሲዳማ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ምድረ ገነት ሽረ -ሲዳማ ቡና
- ሲዳማ ቡና-መቐለ 70 እንደርታ
- ሲዳማ ቡና-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ኢትዮጵያ መድን -ሲዳማ ቡና
- ነገሌ አርሲ-ሲዳማ ቡና
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35 (ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
7. ብሩክ እንዳለ (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ምድረ ገነት ሽረ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‐ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ነገሌ አርሲ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-አዳማ ከተማ
- ሀዲያ ሆሳዕና-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
8. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ17 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ናትናኤል ዳንኤል
- ዘላለም አበበ
- ጸጋዬ ብርሀኑ
- ሲሞን ፒተር
- አማኑኤል ደስታ
- ካሌብ እማንክዋህ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000/ አምስት ሺ/እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
9. ምድረ ገነት ሽረ ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ17 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የምድረ ገነት ሽረ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ስንታየሁ ወለጬ
- ክፍሎም ገ/ሂወት
- ስንታየሁ ወለ
- ሽመክት ጉግሳ
- ተካልኝ ደጀኔ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ /እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
10. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ : ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ17 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- እንዳልካቸው ጥበቡ
- ብሩክ እንዳለ
- ዳዊት ገብሩ
- ኤፍሬም ኃ/ማርያም
- ሙታክብዋ ጆኤል
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
11. አንተነህ ተስፋዬ (ምድረ ገነት ሽረ) ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ17ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 17 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች ሆን ብሎ በክርን ስለመማታቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
12. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር በነበረው የ17ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በቅጣት ላይ የነበረ የክለቡ ተጫዋች ጨዋታው ተጠናቆ ዳኞች ከሜዳ ሳይወጡ አጥር በመዝለል ወደ ሜዳ ከመግባቱም በተጨማሪ ተጫዋቾቹን ተከትሎ ወደመልበሻ ክፍል ስለመሄዱ ሪፖርት ቀርቦበታል።
በመሆኑም ተጫዋቹ ላጠፋው ጥፋት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በቀን ዐ8/04/2018 በደብዳቤ ቁጥር የኢ/ ፕ / ሊ / አ / ማ/4071/18 ለክለቦች ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ክለቡ ብር 25000/ሀያ አምስት ሺህ እንዲከፍል ወስኗል።
13. ሸገር ከተማ ክለቡ በ17ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ ስላለመገኘቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ከለቡ በፈጸመው ጥፋት በፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 1ዐ ተቁ 7 መሰረት ብር 5000/አምስት ሺህ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
14. አሰልጣኝ ስንታየሁ ግድየለው (ሲዳማ ቡና – የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ) ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር በነበረው የ17ኛ ሳምንት ግጥሚያ ጨዋታው ካለቀ በኋላ ወደመልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያሉ በኮሪደር ላይ የጨዋታ አመራሮችን አጸያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። ስለሆነም የቡድን አመራሩ በፈጸሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት 6 / ስድስት ጨዋታ እንዲታገዱና ብር 5000/አምስት ሺህ / እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
15. አቶ ብሩክ ደበበ (ሲዳማ ቡና – ወጌሻ) ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር በነበረው የ17ኛ ሳምንት ግጥሚያ ጨዋታው ካለቀ በኋላ ወደመልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያሉ በኮሪደር ላይ የጨዋታ አመራሮችን አጸያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል። ስለሆነም የቡድን አመራሩ በፈጸሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት 6 / ስድስት ጨዋታ እንዲታገዱና ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
16. ሲዳማ ቡና ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር በነበረው የ17ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ግጥሚያው ካለቀ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎች የተመልካች መቀመጫ ወንበሮችን ወደ ሜዳ ስለመወርወራቸው ሪፖርት ተደርጓል። ስለሆነም ደጋፊዎች በፈጸሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት ክለቡ ብር 25000/ሀያ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።


