የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ተመስገን ተስፋዬ (መቐለ 70 እንደርታ) : አርብ ታህሳስ 10 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ1ዐኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 83 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ዴሲሬ ፓስካል (ነገሌ አርሲ) : ቅዳሜ ታህሳስ 11 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ1ዐኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 75 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
3. ምኞት ደበበ (ፋሲል ከነማ): ቅዳሜ ታህሳስ 11 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ1ዐኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 79 ኛ ደቂቃ ላይየተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቄ 1 (ሠ) እና በተቄ 2 እንዲሁም አንቀፅ 66 ተቁ 1(ሀ) መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3ዐዐዐ /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
4. አብዱሰላም ዩሱፍ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- ወላይታ ድቻ-ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- መቻል-ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ-አዳማ ከተማ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
5. ፋሲል ከነማ ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ1ዐ ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የፋሲል ከነማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 በረከት ግዛው
2 ዮናታን ፍስሃ
3 ምኞት ደበበ
4 ቢኒያም ጌታቸው
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
6. ነገሌ አርሲ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ10 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የነገሌ አርሲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 ናትናኤል ሰለሞን
2 አሸብር ዉሮ
3 ዴሲሬ ፓስካል
4 ዴሲሬ ፓስካል
5 ሮኅቦት ሰላሎ
6 ዳዊት ተፈራ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
7. መቻል ክለቡ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በነበረው የ10ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ቅድመ ስብሰባ ወቅት የክለቡ ተወካይ 20 ደቂቃ አርፍዶ ስላለመምጣቱ ሪፖርት ቀርቦበታል፡፡
በመሆኑም በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 1ዐ ተቁ 8 መሰረት የክለቡ ተወካይ ብር 1ዐዐዐ / አንድ ሺህ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


